የዓመቱን ቀሪ ተግባራት በቀጣይ ሁለት ወራት በተ...

image description
- In ንግደረ    0

የዓመቱን ቀሪ ተግባራት በቀጣይ ሁለት ወራት በተሟላ መልኩ ለማጠናቀቅ ከምንግዜውም በላይ መረባረብ ይኖርብናል ተባለ!

የዓመቱን ቀሪ ተግባራት በቀጣይ ሁለት ወራት በተሟላ መልኩ ለማጠናቀቅ ከምንግዜውም በላይ መረባረብ ይኖርብናል ተባለ!

ግንቦት 6/9/2017 ዓ.ም.

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ዛሬ ባካሄደው የጀነራል ካውንስል የውይይት መድረክ በቀጣይ ቀሪ ሁለት ወራት መፈፀም የሚገባንን ተግባራት በመለየትና መታረም የሚገባቸው ላይ ትኩረት በመስጠት የበለጠ ርብርብ ማድረግ እንደሚጠበቅ የገለፁት የቢሮ የኢንስፔክሽን እና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ስመኘው ተሾመ ሲሆኑ በተለይ በተለያየ ወቅት በሚመለከታቸው ተቋማት የተሰጡንን ግብረ መልሶች በአግባቡ በመለየት ሁሉም የስራ ክፍሎች የሚጠበቅባቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በ9 ወሩ ጠንካራ እና ለውጥ ያመጡ ውጤቶችን ቢሮ ያስመዘገበ መሆኑን የተናገሩት አቶ ስመኘው አሁንም በቀሪ ሁለት ወራት አሉ የምንላቸውን ክፍተቶች በማረም የተሻለ ውጤት ለማምጣት ሁላችንም ልንረባረብ ይገባል ብለዋል፡፡

የቢሮ የሰው ሀብት ልማት እና ስራ አመራር ዳይሬክተር በበኩላቸው በተለይ የፈፃሚውን አቅም በመገንባት እና እያደረግን ያለውን ተቋማዊ ሪፎርም ከግብ ለማድረስ የሰራተኛውን አቅም የመገንባት እና ሰራተኛው እርስ በዕርሱ የሚማርበትን መድረክ ማጎልበት አስፈላጊ በመሆኑ በቀጣይ ትኩረት አድርገን የምንሰራባቸው ናቸው ያሉ ሲሆን ሠራተኛው ያለውን እውቀት ወደ ተቋም በመቀየር ውጤት ማስመዝገብ መጀመራቸውን ገልፀው በቀጣይም የሠራተኛውን ሁለንተናዊ ዕውቀት በአግባቡ በማደራጀት የተሻለ ስራ መስራት ላይ አተኩረን መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

ቢሮ ከዛሬው የፕሮሰስ ካውንስል መድረክ በተጨማሪ የ9 ወር የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማውን በየደረጃው ከሚገኙ የሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments