የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ፥ ከአዲስ አበባ ህብረ...

image description
- In ንግደረ    0

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ፥ ከአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮሚሽን ጋር በመሆን የቅዳሜና እሁድ የገበያ ስፍራዎች አሰራርና አፈጻጸምን ገመገመ፤

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ፥ ከአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮሚሽን ጋር በመሆን የቅዳሜና እሁድ የገበያ ስፍራዎች አሰራርና አፈጻጸምን ገመገመ፤

=========================

አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ግንቦት 6/2017 ዓ/ም

የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ፥ ከአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮምሽን፣ ከክፍለ ከተሞች ንግድ ጽ/ቤቶች እና ህብረት ስራ ጽ/ቤቶች ጋር በመሆን የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች አሰራር በከተማ ደረጃ በተቋቋመ ግብረ-ኃይል በተደረገ የመስክ ስምሪት ገምግሟል።

በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ የተቋቋመ ግብረ-ኃይል በሁሉም ክፍለ-ከተሞች የሚገኙ የቅዳሜና እሁድ የገበያ ስፍራዎች የዋጋ እና የምርት አቅርቦትና ጥራት ቁጥጥር ላይ የመስክ ግምገማ አካሂዶ የተገኙ ግኝቶች ርፖርቶች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል።

ግምገማውን የመሩት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ እና የሬጉላቶሪ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ስመኘው ተሾመ እና የአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮምሽን ምክትል ኮሚሺነር አቶ ሀብተየስ ዲሮ ሲሆኑ፤ ሪፖርት አቅራቢዎች በሁሉም ክፍለ ከተሞች በገበያ ስፍራዎች የተገኙ ግኝቶች ርፖርትን አቅርበዋል። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ እና የሬጉላቶሪ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ስመኘው ተሾመ መንግስት የቅዳሜና እሁድ የገበያ ስፍራዎችን ያመቻቸው የግብርናና የፋብሪካ ምርቶች አቅርቦትን በማሳደግና የዋጋ መናርን በመከላከል የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በመሆኑ በእነዚህ የገበያ ስፍራዎች ነጋዴዎች በተለጠፈ ዋጋ መሸጣቻውን እና የአቅርቦት ጥራት መኖሩን ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ በሸማቹ ህብረተሰብ የሚቀርበውን ቅሬታ መመለስ ግዴታ መሆኑ እና ለዚህም በቅንጅት መስራት የተሻሻሉ የቅዳሜና እሁድ ገብያዎችን ለማምጣት እንደሚረዳ ገልጸዋለ።

የአዲስ አበባ ህብረት ሰራ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር አቶ ሀብተየስ ዲሮ በበኩላቸው ከቀረቡ የመስክ ሪፖርቶች በመነሳት በቅዳሜና እሁድ የገበያ ስፍራዎች የሚታዩ ችግሮችን ለማረም እና በአትክልትና ፍራፍሬ አቅራቢ ነጋዴዎች፣ በሸማች ህብረት ስራ ማህበራትና በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ዘንድ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመሙላት እና የከተማችንን ነዋሪ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ለወደፊት በቅንጅት ጠንክረን መስራት አለብን ሲሉ ገልጸዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments