ቢሮው "የጀመሩ ሳይሆን የጨረሱ ናቸው የሚሸለሙት...

image description
- In ንግደረ    0

ቢሮው "የጀመሩ ሳይሆን የጨረሱ ናቸው የሚሸለሙት" በሚል ርዕስ የአስር ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ፤

ቢሮው "የጀመሩ ሳይሆን የጨረሱ ናቸው የሚሸለሙት" በሚል ርዕስ የአስር ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ፤

=============+++====================

አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ግንቦት 8/2017 ዓ.ም.

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ "የጀመሩ ሳይሆን የጨረሱ ናቸው የሚሸለሙት" በሚል ርዕስ በ2017 በጀት ዓመት የአስር ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ ከአጠቃላይ ሰራተኛውጋ አካሂዷል።

ግምገማውን የመሩት የንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ፣ የግብይትና ገበያ ልማት ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍሰሃ ጥበቡ እና የንግድ ሬጉላቶሪ ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ስመኘው ተሾመ ሲሆኑ፥ የቢሮው እቅድና በጀት ዝግጅትና ግምገማ ዳይሬክተር አቶ መለሰ ሪፖርቱን አቅርበው በተሳታፊዎች ገንቢ ሃሳቦችና ጥያቄዎች ቀርበዋል።

ለቀረቡት ጥያቄዎችና ሃሳቦች ምላሽ የሰጡት የቢሮው ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ከተማችን ዘመናዊ፣ ፍትሃዊና ተወዳዳሪ የንግድ ስርዓት የሰፈነባት የአፍሪካ ግንባር ቀደም ከተማ እንድትሆን ለማድረግ በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል ብለዋል። የሸማቹንና የንግዱን ማሕበረሰብ ጥቅም ለማስከበር እንዲቻል ለግብይት የሚቀርቡ ምርቶችን በማሳደግ የኑሮ ውድነትን ከመከላከል አንጻርና ህገ-ወጥ ንግድ ላይ ክትትልና ቁጥጥር በማካሄድ ፍትሃዊና በውድድር ላይ የተመሰረተ የንግድ ስርዓት ከመገንባት አኳያ በግብይትና ገበያ ልማት ዘርፍም ሆነ በሬጉላቶሪ ዘርፍ ባለፉት አስር ወራት በርካታ ተግባራት መከናወናቸውንና ውጤት ለማምጣት መሰራቱን ገልጸዋል።

በመንግስት በተገነቡ የገበያ ማዕከላት እና በቅዳሜና እሁድ የገበያ ስፍራዎች የኑሮ ውድነትን ለመከላከል የሚያስችሉ የግብርናና የፋብሪካ ምርቶች በስፋት ለገበያ መቅረባቸውን ጠቅሰው ቁጥጥሩ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል።

በኮምኒኬሽን ዘርፍ ቢሮው የሚያከናውናቸውን ተግባራት ከማስተዋወቅ አንጻር የተሰሩ ስራዎች አበረታች መሆናቸውንና ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ገልጸዋል። ባለፉት አስር ወራት የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት፥ ጥንካሬዎችን በማስቀጠልና ድክመቶችን በቀሪ ሁለት ወራት በማረም በከተማችን በንግዱ ዘርፍ ስር-ነቀል ለውጥ ለማምጣት በትኩረትና በህብረት መትጋት እንደሚገባ ገልጸዋል።

የግብይትና ገበያ ልማት ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍሰሃ ጥበቡ በበኩላቸው የስራ ቦታን ለስራ ምቹ ከማድረግ አኳያና የቢሮውን መዋቅር ከማዘመን እና የቢሮው መዋቅርና አደረጃጀት ዘመኑን የዋጀና በቴክኖሎጂ የበለጸገ እንዲሆን ከማድረግ አንጻር ባለፉት አስር ወራት የተሰሩ ስራዎች አበረታች መሆናቸውንና ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ አንስተዋል። በከተማችን የሚገኙ ነጋዴዎች ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የተመዘገቡ ነጋዴዎች እንዲሆኑ በማድረግ ከንግድ ምዝገባና ፈቃድ አንጻር ሰፊ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል።

የንግድ ሬጉላቶሪ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ስመኘው በበኩላቸው በከተማችን የሚካሄደው የንግድ ስራ በግልጽ ውድድር ላይ የተመሰረተና ጤናማ እንዲሆን በተደራጀና በተጠናከረ አግባብ በመምራት ሥር ነቀል ለውጥ ለማምጣት እንዲቻል፥ ህገ-ወጥ የንግድ ተግባራትን በመከላከል የንግድ ክትትል እና ቁጥጥር ተግባራትን በማጠናከር በህገ-ወጦች ላይ ተገቢ እና ሊያስተምር የሚችል እና በንግድ አዋጅ፣ ደንብ እና መመሪያ መሰረት ደረጃውን የጠበቀ አስተዳደራዊ እና ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ የንግድ ህጋዊነት ለማስከበርና ህገወጦችን ወደ ህጋዊነት ለመመለስ የተሻለ አፈጻጸም እንዲኖር እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments