በከተማ አስተዳደራችን በሚገኙ ሁሉም ክ/ከተሞችና...

image description
- In ንግደረ    0

በከተማ አስተዳደራችን በሚገኙ ሁሉም ክ/ከተሞችና ወረዳዎች "የብልፅግና ጉዟችንና የንግዱ ማህበረሰብ ሚና" በሚል መሪ ሀሳብ ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ውይይት መካሄድ ጀመረ፤

በከተማ አስተዳደራችን በሚገኙ ሁሉም ክ/ከተሞችና ወረዳዎች "የብልፅግና ጉዟችንና የንግዱ ማህበረሰብ ሚና" በሚል መሪ ሀሳብ ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ውይይት መካሄድ ጀመረ፤

============+++=========

አዲስ አበባ ግንቦት 10/ 2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ሁሉም ክ/ከተሞችና ወረዳዎች "የብልፅግና ጉዟችንና የንግዱ ማህበረሰብ ሚና" በሚል መሪ ሀሳብ ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ውይይት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በአገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄደውን ይህንን የውይይት መድረክ በከተማ ደረጃ ተገኝተው ያስጀመሩት የኢፌድሪ ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚንስተር ክቡር ዶክተር ካሳሁን ጎፌ በውይይት መድረኩ ማስጀመሪያ ላይ ባደረጉት ንግግር፥ አገራችን የጀመረችውን የብልጽግና ጉዞ ለማስቀጠልና አሁናዊና መጻኢ እድገቷን ከዳር ለማድረስ የንግዱ ማህበረሰብ ሚና ላቅ ያለ መሆኑን ጠቅሰው፥ ለዚህም የንግዱ ማህበረሰብ አሉብኝ በሚላቸው ተግዳሮቶች ዙርያ መወያየትና መመካከር አስፈላጊነቱ ከፍ ያለ ነው ብለዋል።

ዶ/ር ካሳሁን ከንግድ ሚኒስተር ጀምሮ በየደረጃው የሚገኙ የንግድ ተቋማት ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ሊኖራቸው የሚገባው ግንኙነት እንደ አይጥና ድመት የጎሪጥ የመተያየት ሳይሆን፣ እንደ ቤተሰብ መቀራረብና መወያየትን በማስቀደም ነግዶና አትርፎ አገር እንዲያቀና አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ ተገቢ ነው ብለዋል።

በአገር አቀፍ ደረጃ ከ3 ሚሊዮን በላይ፣ በከተማ አስተዳደራችን ከመቶ ዘጠና ሺህ በላይ የንግዱ ማህበረሰብ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ በተዘጋጀው መድረክ ላይ እንደሚሳተፍ በመድረኩ ላይ ተገልጿል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments