
በከተማችን የሚስተዋለውን ወቅታዊ የዋጋ ንረት ለማረጋጋት ያለም የከተማው የንግድ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ግምገማ ተካሄደ፤
በከተማችን የሚስተዋለውን ወቅታዊ የዋጋ ንረት ለማረጋጋት ያለም የከተማው የንግድ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ግምገማ ተካሄደ፤
=============+++=========
አዲስ አበባ ግንቦት 12፥ 2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ የሚስተዋለውን ወቅታዊ የዋጋ ንረት ለማረጋጋት ያለም የከተማው የንግድ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ግምገማ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ተካሂዷል።
ግምገማውን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ሲሆኑ፥ በግምገማው ላይ የተሳተፉት ባለድርሻ ተቋማት፥ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ፣ የአዲስ አበባ ኢንዱስትሪ ቢሮ፣ የአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮሚሽን፣ የአዲስ አበባ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን፣ የአዲስ አበባ ከተማ ግብርና እና የከነማ ፋርማሲ ናቸው።
በግምገማው ላይ በመሠረታዊ የፍጆታ ምርቶች ወቅታዊ የዋጋ ንረት መንስዔዎች እና ዘላቂ መፍትሔዎች ላይ ከተሳታፊዎች በርካታ ሃሳቦች ቀርበዋል።
ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ በከተማ ደረጃ የሚስተዋለውን መሠረታዊ የፍጆታ ምርቶች የዋጋ ንረት መንስዔዎቹን በመለየት አቅርቦታችንን በማሳደግና በማስፋት መሠረታዊ የፍጆታ ምርቶችን በህብረት ስራ ኮሚሽን የሸማቾች ሱቆችና በንግድ ስራ ኮርፖሬሽን ሱቆች በስፋት በማቅረብና የአቅርቦት እጥረት እንዳይኖር በማድረግ የዋጋ ማረጋጋት መፍጠር ላይ በጋራ ልንሰራ ይገባል ብለዋል። በመጨረሻም ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ መሠረታዊ የፍጆታ ምርቶች ወቅታዊ የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር ባለድርሻ ተቋማት ሊሰሩ የሚገባቸው ተግባራት ላይ አቅጣጫ አስቀምጠው የውይይቱ መጠናቀቅ ሆኗል።
In order to stabilize the current inflation that is seen in our city, an evaluation of the city's business sector stakeholders was held.
=============+++=========
Addis Ababa May 12, 2017 E. ም
In order to stabilize the current inflation that is seen in Addis Ababa city, the assessment of the city's business sector stakeholders has been conducted by Addis Ababa City Administration Commercial Office.
The review was led by the Addis Ababa City Administration Business Bureau, Mrs. Habiba Siraj. The stakeholders that participated in the review are Addis Ababa Business Bureau, Addis Ababa Industry Bureau, Addis Abeba Cooperative Works Commission, Addis Abba Business Works Corporation, Addis Abeaba City Agriculture and Kenema Pharmacy.
In the review, many ideas were presented from the participants on the current causes of inflation and sustainable solutions.
Her excellency Mrs. Habiba has said that we should work together to create price stability by identifying the causes of the inflation of basic consumer products, increasing and expanding our supply of basic consumer products by providing them to the Cooperative Labor Commission shops and business corporations shops and to avoid supply shortage. Finally, the discussion has been concluded by Her excellency Mrs. Habiba put direction on what stakeholders should do to control the current inflation of basic consumer products.
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments