
"የተለወጠ አዕምሮ ለበለጸገች አገር!" በሚል መርህ የአመለካከት (Mindset) ማበልጸጊያ ስልጠና ተሰጠ፤
"የተለወጠ አዕምሮ ለበለጸገች አገር!" በሚል መርህ የአመለካከት (Mindset) ማበልጸጊያ ስልጠና ተሰጠ፤
==================================================================
አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ፣ ግንቦት 14/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ "የተለወጠ አዕምሮ ለበለጸገች አገር!" በሚል መርህ የአመለካከት (Mindset) ማበልጸጊያ ስልጠና ለሁሉም ሰራተኞቹ ሰጥቷል።
#ስልጠናውን የሰጡት ዶ/ር ናም ፒል ሁዋን አስተሳሰብና አመለካከትን ማበልጸግ የራስን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ የኑሮ ደረጃ ከመቀየር ባሻገር የማህበረሰብንና የአገርን እድገትና ብልጽግና ለማፋጠን ያለውን ሚና ከአስከፊ የድህነት ወለል ተነስታ እስከ ዓለም የኢኮኖሚ ቁንጮነት የደረሰችውን የደቡብ ኮርያን ተሞክሮ በማሳያነት በማንሳት ለሰልጣኝ ሰራተኞች አነቃቂ ስልጠና ስጥተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በበኩላቸው ደቡብ ኮርያውያን በአገር አቀፍ ደረጃ የገጠማቸውን ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ተግዳሮት እንደ መልካም ዕድል በመቀበል፣ ውድቀትን የመማር እድል አድርገው በመመልከት እና እንቅፋቶችን በፅናት በማለፍ ሁሉም ዜጋ ለስራ ፈጠራ በመትጋት እና አዳዲስ ሀሳቦችን በማመንጨት በአገር ደረጃ ልማትን ማስመዝገባቸው ለኛ ትምህርት ሊሆን ይገባል፤ ከእነሱ የአገር ፍቅርንና ለአገር መቆምን ልንማር ይገባል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የሰው ሀብት ልማት ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል በበኩላቸው ለአመለካከት እድገትና ልማት እንዲህ ያሉ ስልጠናዎችን በተደጋጋሚ ማዘጋጀት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው፤ የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ስልጠናዎችን ማዘጋጀቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments