
የቢሮው ሸማች መብት ጥበቃ ከ11ዱም ክፍለ ከተማ አመራርና ቡድን መሪዎች ጋር በመሆን የ10 ወር ስራ አፈፃፀም ላይ ውይይት አድርጓል
የቢሮው ሸማች መብት ጥበቃ ከ11ዱም ክፍለ ከተማ አመራርና ቡድን መሪዎች ጋር በመሆን የ10 ወር ስራ አፈፃፀም ላይ ውይይት አድርጓል
==================
አዲስ አበባ ፡-ግንቦት19/ 2017 ዓም
አዲድ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ሸማች መብት ጥበቃ ከ11ዱም ክፍለ ከተማ አመራርና ቡድንመሪዎች ጋር በመሆን የ10 ወር ስራ አፈፃፀም ላይ ውይይት አድርጓል
በዛሬው እለት በተደረገው ውይይት የንግድ ኢንስፔክሽን ሪጉላቶሪ ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ስመኘው ተሸመ እንደገለፁት ዳይሬክቶሬቱ በ10ወር ውስጥ ሸማች አደረጃጀት ያለበት ደረጃ ፤ክትትልና ድጋፍ አንፃር ፤ከሚቀርቡ ቅሬታዎች በአዋጅ ቁጥር 813/2006 አኳያ የተከናወኑ ጠንካራ ደካማ ጎን ላይ በመተጋገዝ ከሸማቾች መብት ጥበቃ ማኅበር ጋር መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
የሸማች መብት ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ አቶ መሐመድ አላቦ ከክፍለ ከተማ አመራሩና ቡድን መሪዎች ጋር በቀጣይ ለሸማች ማኅበረሰቡን በመተጋገዝ ብልሹ አሰራሮችን እና መልካም አስተዳደር ላይ መስራት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments