
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ምክር ቤት የንግድ እንዱስትር እና ቱርዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአድስ አበባ ንግድ ቢሮን የ10 ወራት ዕቅድ አፈጻፀም እየገመገመ ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ምክር ቤት የንግድ እንዱስትር እና ቱርዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአድስ አበባ ንግድ ቢሮን የ10 ወራት ዕቅድ አፈጻፀም እየገመገመ ነው።
======================================================
ግንቦት 21/2017 ዓ.ም
በእለቱም የቢሮው የ2017 በጀት ዓመት ዋና ዋና ግቦች የ10ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ተቋሙ የንግድ ስርዓቱን ዘመናዊ ቀልጣፋ፣ፍትሀዊና ተደራሽ ለማድረግ ተቋማዊ ሪፎርም አድርጎ ወደ ስራ መግባቱን የቢሮው ሀላፊ #ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ገልፀዋል።
ቋሚ ኮሚቴው በሱፐር ቪዥኑ ትኩረት ካደረገባቸው ጉዳዮች መካከል የተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ፣የተገልጋይ ህዝብ እርካታ እንዲሁም ቅሬታና አቤቱታ፣ተቋሙ ከሌሎች ተቋማት ጋር ያለው ቅንጂታዊ አሰራር፣የውስጥና የውጭ ኦዲት ግኝት ማስተካከያ ፣ የሚቀርቡ ምርቶች ጥራትና በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት ፣ የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት የተወሰደ እርምጃ፣ ህገወጥ ንግድን ለመከላከል የተሰሩ ስራዎች እንዲሁም አዲስ የተገነቡ የሰብልና አትክልት መሸጫ ቦታዎች ያሉበት ሁኔታ የሚሉት ተጠቃሽ ናቸው።
ንግድ ቢሮው የከተማው የጀርባ አጥንት መሆኑን የገለፁት የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ #አቶ ጋትዌች ዎር የኑሮ ውድነቱን ለመቀነስና ህገወጥ ነጋዴዎችን ወደ ህጋዊነት ለማምጣት የተሰራውን ስራ አድንቀዋል።
የተከበሩ አቶ ጋትዌች አክለውም ንግድ ቢሮው የገበያ ማዕከላት ለተቋቋሙለት አላማ ትኩረት እንዲሰጡ ማድረግ እንዲሁም ጠንካራ የሆነ ግንዛቤ ፈጠራና ኮሙኒኬሽን ግንባታ ላይ ከዚህ የበለጠ ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments