
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ፍሰሀ ጥበቡ የተመራ ልዑክ በጋሞ ዞን አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ በሞዴል አርሶ አደሮች የለማ የጓሮ አትክልትና የሙዝ እርሻ ጎበኘ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ፍሰሀ ጥበቡ የተመራ ልዑክ በጋሞ ዞን አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ በሞዴል አርሶ አደሮች የለማ የጓሮ አትክልትና የሙዝ እርሻ ጎበኘ።
በአዲስ አበባ ፤ ግንቦት 23/2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ፍሰሀ ጥበቡ ከድህነት ማምለጫው መንገድ ጠንክሮ መስራት ነው በማለት እርሻችንን በማዘመንና የገበያ ትስስርን በመፍጠር የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑንን ገልጸዋል ።
የገበያ ትስስር መፍጠሩ አርሶ አደሩን በብዙ ያግዛል ያሉት አቶ ፍሰሀ አርሶ አደሩ ያመረተውን ምርት በትኩሱ ገበያ ለማድረስ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሠራ ነው ብለዋል።
የጋሞ ዞን ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሰላማዊት ቦዳ ኑሮ ውድነትን ለመቀነስና ገበያውን ለማረጋጋት ትኩረት ተሠጥቶ እየተሠራ መሆኑን ገልፀው አርሶ አደሮች ያመረቱትን ምርት ያለ እንግልት የሚሸጡበት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር እየተሠራ ነው ብለዋል ።
የአርባምንጭ ከተማ ነጋዴዎች ማህበር አባል የሆኑት አቶ አክሊሉ አድማሱ ከዚህ ቀደም ብዙ እንግልት መኖሩን ገልፀው አሁን ላይ በተመቻቸው ገበያ ትስስር ውጤታማ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑንን ገልጸዋል ።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments