ቢሮው የንግድ ድርጅቶች የበር ለበር ክትትልና ቁ...

image description
- In ንግደረ    0

ቢሮው የንግድ ድርጅቶች የበር ለበር ክትትልና ቁጥጥር ስራዎችን ለማከናወን ያበለጸገውን የOnline መከታተያና መቆጣጠርያ ቴክኖሎጂ ማስጀመሪያ መርሃግብር አካሄደ፤

ቢሮው የንግድ ድርጅቶች የበር ለበር ክትትልና ቁጥጥር ስራዎችን ለማከናወን ያበለጸገውን የOnline መከታተያና መቆጣጠርያ ቴክኖሎጂ ማስጀመሪያ መርሃግብር አካሄደ፤

============+++===========

አዲስ አበባ:- ግንቦት 26 ቀን 2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የንግድ ድርጅቶች የበር ለበር ክትትልና ቁጥጥር ስራዎችን ለማከናወን ያበለጸገውን የOnline መከታተያና መቆጣጠርያ ቴክኖሎጂ ማስጀመሪያ መርሃግብር በኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል አካሄዷል። የቢሮ በላ ድርሻ አከለት የክ/ከተማና የወረዳ የንግድ ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የንግድ ክትትልና ቁጥጥር ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች በተሳተፉበት በዚህ የቴክኖሎጂ ማስጀመሪያ መርሃግብር ላይ ተገኝተው የማስጀመሪያ ንግግር ያደረጉት የአዲስአበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ 'ንግድ ቢሮ ለንግዱ ማህበረሰብ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ቀልጣፋ፣ ዘመናዊና ዘመኑን የዋጁ እንዲሆኑ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ገልጸው፤ እስካሁን ካበለጸጋቸው ቴክኖሎጂዎች በተጨማሪ የንግድ ድርጅቶች የበር ለበር ክትትልና ቁጥጥር ስራ በቴክኖሎጂ የታገዘ እንዲሆን ማድረግ የሚያስችል ቴክኖሎጂ መበልጸጉን ገልጸዋል።

ይህ ቴክኖሎጂ የንግድ ድርጅቶች የበር ለበር ክትትልና ቁጥጥር ስራ ዘመናዊና ቀልጣፋ እንዲሆን ከማድረጉም ባሻገር ከብልሹ አሰራር የጸዳ እንዲሆን እንደሚረዳ ተናግረዋል።

በዚህም መሰረት በPilot project ደረጃ በጉለሌና ቦሌ ክ/ከሞች ሲተገበር የቆየው የዚህ ቴክኖሎጂ ትግበራ ወደ ሁሉም ክ/ከተሞች እንዲሰፋ መወሰኑንና ተግባራዊነቱ ከነገ እንደሚጀምር ገልጸዋል።

በተጨማሪም ከመንደር ቁጥጥር አሰራር መመርያ 159/16 አተገባበር አኳያ እየታዩ ያሉ ጥንካሬዎችና የተስተዋሉ ክፍተቶች፣ ከምሽት የንግድ ድርጅቶች ቁጥጥርና አሰራር መመሪያ 185/17አንጻርና ከቅዳሜና እሁድ ገበያዎች ምርት አቅርቦት፣ አሰራርና ቁጥጥር አንጻር እየታዩ ያሉ ጥንካሬዎችና ክፍተቶች በመድረኩ ላይ በተሳታፊዎች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል። መልስና ማብራርያ ለሚሹ ጥያቄዎች በቢሮ ኃላፊዋ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ፣ በሬጉላቶሪ ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ስመኘውና በግብይትና ገበያ ልማት ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍስሐ መልስና ማብራርያ ተሰጥቶባቸዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments