በአዲስ አበባ ከተማ ቀጣይነት ያለው ህጋዊ የንግ...

image description
- In ንግደረ    0

በአዲስ አበባ ከተማ ቀጣይነት ያለው ህጋዊ የንግድ ስርዓትን ለመዘርጋት በከተማ አስተዳደሩ የሚደረገውን ተግባር ውጤታማ በማድረግ ረገድ ጥምር የንግድና ገቢዎች ህግ ማስከበር ግበረ-ኃይል የተሻለ ለውጥ እያስመዘገበ መምጣቱ ተገለፀ።

በአዲስ አበባ ከተማ ቀጣይነት ያለው ህጋዊ የንግድ ስርዓትን ለመዘርጋት በከተማ አስተዳደሩ የሚደረገውን ተግባር ውጤታማ በማድረግ ረገድ ጥምር የንግድና ገቢዎች ህግ ማስከበር ግበረ-ኃይል የተሻለ ለውጥ እያስመዘገበ መምጣቱ ተገለፀ።

***

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 25 ቀን 2017 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ ግንቦት 25 ቀን 2017 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በህግ ማስከበርና ቁጥጥር ንዑስ ኮሚቴ በ11 ወራት ውስጥ የተከናወኑ የግብረ ኃይል ዋና ዋና ተግባራት ሪፖርትና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች ላይ በሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት አደረገ። በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋውና የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅና የተለያዩ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በውይይቱ ላይ እንደገለጹት ህጋዊ የንግድ ስርዓትን ለመፍጠር በህግ ማስከበር ረገድ አመርቂ ለውጦች በ11 ወራት ውስጥ በተሻለ ሁኔታ መምጣት መቻሉን ገልፀው የተፈለገው ውጤት እስኪመጣ ድረስ በቀጣይነት የቁጥጥር ስራዎችን በማጠናከር ህዝቡን ለምሬት የሚዳርጉ በተለይ መሰረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች ላይ ቁጥጥርና ክትትል በማድረግ የበለጠ ሥራውን ማጠናከር ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫ እንደሆነ ገልፀዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ በፍጆታ ዕቃዎች ዙሪያ እየተስተዋለ ያለ የዋጋ ንረት ጉዳይ የአቅርቦት እጥረት ምክንያት ሳይሆን የህገ-ወጥ ነጋዴዎች አሻጥርና ሴራ እንደሆነና በመሰል ነጋዴዎች ላይ ደግሞ ቁጥጥርና ክትትል በማድረግ በቀጣይነት እንደ ከተማ ንግድ ቢሮ እርምጃ እንደሚወሰድ የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ገልፀዋል።

ህጋዊ የንግድ ስርዓቱን በተፃረረ አኳኋን ያልተገባ ተግባር ላይ በመሳተፍ ህዝብን ለማማረር የሚሰሩ አካላትን ከዚህን ቀደም በቁጥጥር ስር በማዋልና ምርመራ በማጣራት ለሚመለከተው የፍትህ አካል በማቅረብ በህግ አግባብ እንዲቀጡ የተደረገ መሆኑን የተናገሩት የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው በመሰል አካላት ላይ ቀጣይነት ባለው አኳኋን ህግ የማስከበር ስራን ትኩረት በመስጠት እንደሚሰራም ገልጸዋል።

ዘርፈ ብዙ ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎች ሲከናወንባት የነበረችው አዲስ አበባ ከተማ ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ህጋዊ የንግድ ስርዓትን ለመፍጠር በህገ-ወጥ ነጋዴዎች ላይ በሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተደረገ ቁጥጥርና በተወሰደ የማያዳግም እርምጃ አመርቂ ስራዎች መሰራታቸው የተገለፀ ሲሆን አሁንም ድረስ ሆን ተብሎ በአሻጥር የኑሮ ውድነት እንዲባባስ እየሰሩ ባሉ ህገ-ወጥ ነጋዴዎች ላይ በቀጣይነት በተጠናከረ ሁኔታ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገልጿል።

በአዲስ አበባ ከተማ ህገ-ወጥ የንግድ ስርዓትን በመታገል ህጋዊ የንግድ ስርዓትን ለመዘርጋት በከተማ አስተዳደሩ የሚሰራውን ስራ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር ጥምር የንግድና ገቢዎች የህግ-ማስከበር ግብረ-ኃይል የተሻሉ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ የውይይቱ ተሳታፊዎች አንስተዋል።

*

ዘገባ፦ ዋ/ሳጅን ጤናው ፈጠነ

*

ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦

በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice

በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice

በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission

በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice

ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/

“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”

“Protect with courage, Serve with Compassion!”


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments