
ብቃት ያለው ሲቪል ሰርቪስ ለኢትዮጵያ ብልፅግና”በሚል ርዕስ የሠራተኞች ውይይት ተካሄደ
”ብቃት ያለው ሲቪል ሰርቪስ ለኢትዮጵያ ብልፅግና”በሚል ርዕስ የሠራተኞች ውይይት ተካሄደ"
አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ፣ ግንቦት 28 ቀን 2017 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ሠራተኞች ”ብቃት ያለው ሲቪል ሰርቪስ ለኢትዮጵያ ብልፅግና" በሚል መሪ ሀሳብ ውይይት አካሂደዋል፡፡
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጀማሉ ጀንበር በቪዲዮ ባስተላለፉት የውይይት መነሻ ሰነድ፤ ከለውጡ ወዲህ የተከናወኑ የሪፎርምና የልማት ሥራዎችን፣ እንዲሁም በኢኮኖሚያዊ፣ በማህበራዊ እና በፖለቲካዊ ዘርፎች የተመዘገቡ ስኬቶችን አብራርተዋል።
በአገልግሎት አሰጣጥና በብልሹ አሰራር አሁንም ያልተሻገርናቸው ችግሮች መኖራቸውንና ችግሮቹን ለማረም እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት መኖራቸውን በሰነዱ ተጠቁሟል።
በቀጣይ ከሚሠሩ የትኩረት አቅጣጫዎች መካከል፤ የፈፃሚውን ብቃት ማረጋገጥ እና አቅም መገንባት፣ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማሳደግ፣ ሌብነትና ብልሹ አሰራርን በተደራጀ አግባብ መታገል፣ የሽልማትና ዕውቅና አሰጣጥ ስርዓትን ማጠንከር፣ እንዲሁም የዲጂታል አንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥን ተግባራዊ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ ዶ/ር ጀማሉ አመላክተዋል።
በመድረኩ የቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ገማቹ እና ም/ብሮ ኃላፊ አና የንግድ ሪጉራቶር ዘርፊ ኃላፊ አቶ ስመኘዉ ተሾመ የመንግስት ሰራተኞች በተገኙበት መነሻ ሰነድ ቀርቦ ውይይት እየተካሄደ ነው።
ውይይቱ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በሪፎርምና በልማት ሥራዎች ላይ እንዲሁም በኢኮኖሚያዊ፣ በማህበራዊ እና በፖለቲካዊ ዘርፎች ላይ የተመዘገቡ ስኬቶችን የሚያስገነዝብና በቀጣይ በሚከናወኑ የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር ስራዎች እንዲሁም የሌብነትና ብልሹ አሠራርን ታግሎ በማስተካከል ረገድ የመንግስት ሰራተኛው የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እንዲወጣ የሚያስችል ነው ብለዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments