የአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ንግድ ጽ/ቤት የጽ/...

image description
- In ንግደረ    0

የአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ንግድ ጽ/ቤት የጽ/ቤት የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የሰራውን የሪፎርም ስራ አስመረቀ።

የአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ንግድ ጽ/ቤት የጽ/ቤት የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የሰራውን የሪፎርም ስራ አስመረቀ።

========================================================================

አድስ አበባ ንግድ ብሮ ሰኔ 5/2017

የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ እንደተናገሩት የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓቱን በማዘመን ፍትሃዊ አገልግሎት ለመስጠትና በአገልግሎት አሰጣጡ የረካ ማህበረሰብ ለመፍጠር ስማርት ሲቲ እየገነባን ባለንበት ወቅት የአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ንግድ ጽ/ቤት የሰራው ቢሮንና አገልግሎት አሰጣጥን የማዘመን ስራ የሚደነቅና ለሌሎች አራዓያ የሚሆን ነው ብለው ክፍለ ከተማ ላይ የተፈጠረው የሰራተኞች መነሳሳትና አሰራርን የማዘመን ስራ እስከ ወረዳ ድረስ መውረድ አለበት ብለዋል፡፡

ፈጠራ የታከለበትና በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት አሰጣጥ መመልከታቸውን የገለጹት ወ/ሮ ሀቢባ ለስራው መሳካት ተሳትፎ ያደረጉትን አካላት አመስግነው በቀጣይ ተቋማቸው እስከ ወረዳ ድረስ ድጋፍና ክትትል የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments