የምሽት ንግድ ስራዎች መመሪያ አተገባበር የሚገኝ...

image description
- In 2ኛው ከተማ ዓቀፍ "የኢትዮጵያን ይግዙ"    0

የምሽት ንግድ ስራዎች መመሪያ አተገባበር የሚገኝበት ሁኔታ በከፍተኛ አመራሩ ቅኝት ተካሄደ፤

የምሽት ንግድ ስራዎች መመሪያ አተገባበር የሚገኝበት ሁኔታ በከፍተኛ አመራሩ ቅኝት ተካሄደ፤

===========≥==========≥=============≥==========≥========

አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሐምሌ 15/2017 ዓ.ም.

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተማችን ዓለም አቀፋዊትና ተወዳዳሪ የንግድ ከተማ እንድትሆን የሚረዳ የምሽት ንግድ ደንብ ቁጥር 185/17 አጽድቆ ወደስራ መገባቱ ይታወሳል። በዚሁ መሠረት የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሠላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ልድያ ግርማና ከሌሎች የከተማና የክ/ከተሞች አመራሮችጋ በመሆን በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የምሽት ንግድ ስራዎች ደንብ ቁጥር 185/17 አተገባበር የሚገኝበት ሁኔታ ቅኝት አካሂደዋል።

በቅኝቱ ወቅትም በክ/ከተማው ለሚገኙ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት በምሽት ንግድ ደንብ ቁጥር 185/17 ዙርያ የግንዛቤ ፈጠራ ስራ በበቂ ሁኔታ መሰራቱንና የንግዱ ማህበረሰብም ደንቡን በመተግበር ረገድ እያሳየ የሚገኘው ተነሳሽነት ይበል የሚያሰኝ መሆኑን መመልከት ተችሏል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments