ቢሮው በማኬባ ቴክኖሎጂ ስርጭት እየተተገበረ ያለ...

image description
- In 2ኛው ከተማ ዓቀፍ "የኢትዮጵያን ይግዙ"    0

ቢሮው በማኬባ ቴክኖሎጂ ስርጭት እየተተገበረ ያለውን የመሰረታዊ ሸቀጦች ስርጭት አተገባበር ውጤታማነት ላይ ውይይት አደረገ

ቢሮው በማኬባ ቴክኖሎጂ ስርጭት እየተተገበረ ያለውን የመሰረታዊ ሸቀጦች ስርጭት አተገባበር ውጤታማነት ላይ ውይይት አደረገ

==============================

አዲስ አበባ ፡-ሐምሌ 17ቀን 2017 ዓም

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በማኬባ ቴክኖሎጂ ስርጭት እየተተገበረ ያለውን የመሰረታዊ ሸቀጦች ስርጭት አተገባበር ውጤታማነት ላይ ውይይት አደረገ

ጥናቱን ያቀረቡት የገበያ መረጃ ጥናት ፕሮሞሽን ቡድን መሪ አቶ እንግዳው ተገኝ በከተማው የሚካሄደው የግብይት ስርዓት የሚመራበት አግባብ ህብረተሰቡን ለመጠቀም የታለመ መሆኑና ዘመኑን ያማከለ በቴክኖሎጂ የዘመነ መሆን እንደሚገባ በጥናቱ አቅርበዋል

የቢሮው የንግድ ግብይትና ገበያ ልማት ዘርፍ አቶ ፍስሀ ጥበቡ የማኬባ ቴክኖሎጂ ስርጭት ቴክኖሎጂው በብዙ መንገድ እያደገ የመጣና ኢኖቬሽን ፤በነኢንሳ የተረጋገጠ መሆኑንና ፤ሌሎችም ካሉ ሚጋበዙ መሆኑንና ችግሩ ግን የዘይት እና ስኳር የአቅርቦት እጥረቱ የጋራ ችግር እንደሆነ ተናግረዋል

የቢረው ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ የጥናቱ ዋና አላማ ቴክኖሎጂውን ማስቀጠል መሆኑን ገልፀው ንግድ ቢሮ ከዘመናዊነት ውጭ ወደ ዋላ እንደማይመለስ አሳስበዋል ::


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments