
ቢሮው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ጋር የቅንጅት ስራዎች ማሳለጫና መግባቢያ ትስሰር ሰነድ ተፈራረመ፤
ቢሮው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ጋር የቅንጅት ስራዎች ማሳለጫና መግባቢያ ትስሰር ሰነድ ተፈራረመ፤
===========##============
አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ፥ ሀምሌ 17 2017
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ጋር የቅንጅት ስራዎች ማሳለጫና መግባቢያ ትስሰር ሰነድ ተፈራርሟል።
የንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ የሁለቱ ተቋማት ተልዕኮዎችና ተግባራት በጋራ የሚከወኑ በመሆናቸውና ሁለቱም ተቋማት ለአንድ ከተማ ብልጽግና የሚሰሩ በመሆናቸው፤ በንግዱ ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ በ2018 በጀት ዓመት በጋራ በመስራት ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ አሳስበዋል።
በቢሮው የንግድ ግብይትና ገበያ ልማት ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍሰሃ ጥበቡ በበኩላቸው ከተማችንን በጋራ ለማልማትና ቀልጣፋ፣ ፍትሃዊና በውድድር ላይ የተመሰረተ የንግድ ስርዓትን በከተማችን ለመገንባት የግብይት ሰንሰለቱን ጤናማ ለማድረግ በጋራ መስራት ጠቃሚ መሆኑን ገልጸዋል።
በመጨረሻም ከንግድ ቢሮ በኩል በክሪላንስ፣ ዘርፍ ለውጥ፣ አድራሻ ለውጥ ዙርያ ሲስተሙ እንደማያሳይ በመግለጽ እንዲሻሻል ለቀረቡ ጥያቄዎች ሲስተሙን በጋራ በመፈተሸ ችግሮቹን ለመቅረፍ እንደሚሰሩ ከገቢዎች የመጡ ልኡካን ገልጸዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments