ቢሮው የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀምን መ...

image description
- In 2ኛው ከተማ ዓቀፍ "የኢትዮጵያን ይግዙ"    0

ቢሮው የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀምን መነሻ በማድረግ፣ ለቢሮው ዳይሬክቶሬቶች፣ ለክፍል ከተሞችና ወረዳዎች ንግድ ጽ/ቤቶች እንዲሁም ለቢሮው ሰራተኞች የዕውቅናና ሽልማት መርሃ ግብር አካሄደ።

ቢሮው የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀምን መነሻ በማድረግ፣ ለቢሮው ዳይሬክቶሬቶች፣ ለክፍል ከተሞችና ወረዳዎች ንግድ ጽ/ቤቶች እንዲሁም ለቢሮው ሰራተኞች የዕውቅናና ሽልማት መርሃ ግብር አካሄደ።

‎=====+=====+===+===+======

‎የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃጸምን መነሻ በማድረግ፣ ለቢሮው ዳይሬክቶሬቶች፣ ለክፍል ከተሞችና ወረዳዎች ንግድ ጽ/ቤቶች እንዲሁም ለቢሮው ሰራተኞች ዕውቅናና ሽልማትን አከናውኗል።

በእውቅናና ሽልማት መርሃ-ግብሩ ላይ ገለጻ ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ገመቹ ይህ የእውቅናና ሽልማት መርሐ-ግብር ዋና ዓላማው በ2017 በጀት ዓመት የነበረውና የስራ ተነሳሽኘትና ግለት በ2018 በጀት ዓመት በማስቀጠል የተሻለ አፈጻጸም እንዲኖር ለማድረግ መሆኑን ገልጸዋል።

ለቢሮው ሰራተኞች የተዘጋጀውን ሽልማት የሰጡት የንግድ ሬጉላቶሪ ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ስመኘው ተሾመና የቢሮው ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ገመቹ ሲሆኑ፤ ከሁሉም ዳይሬክቶረቶች 1ኛ የወጡ ባለሙያዎች የምስክር ወረቀትና የቦንድ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ለወራዳዎች ሽልማትና እውቅናን የሰጡት በቢሮው የግብይትና ገበያ ልማት ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍሰሃ ጥበቡና የንግድ ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አበበ ጉተማ ሲሆኑ ከሁሉም ክ/ከተሞች አንደኛ ለወጡ ወረዳዎች ላፕቶፕ፣ ሁለተኛና ሦስተኛ ለወጡ ሰርተፍኬት ተሰጥቷቸዋል።

ለማዕከል ዳይሬክቶሬቶችና ለክ/ከተሞች ንግድ ጽ/ቤቶች ሽልማት ያበረከቱት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅና የአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር የንግድ እንዱስትሪ እና ቱርዝም ቋየም ኮምቴ አቶ ጋክቱል ውር ሲሆኑ፤

ከዓላማ ፈጻሚ ዘርፍ ዳይሬክቶሬቶች:-

1ኛ. የግብይት ማስፋፍያ ዳይሬክቶሬት

2ኛ. የኢንስፔክሽንና ሬጉላቶሪ ዳይሬክቶሬት

2ኛ.የምዝገባና ፈቃድ ዳይሬክቶሬት፣

3ኛ. የገበያ ጥናትና ፕሮሞሽን ዳይሬክቶሬት

አበይት ተግባራት ዘርፍ ዳይሬክቶሬቶች

1. የሰው ሀብት ልማት እና ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት

2. የለውጥ ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት

3. የኢንፎርሜሽን ዳይሬክቶሬት

ሲሆኑ

ከክ/ከሞች

1. አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ንግድ ጽ/ቤት

2. አራዳ ክ/ከተማ ንግድ ጽ/ቤት

2. የካ ክ/ከተማ ንግድ ጽ/ቤት

3. ቂርቆስ ክ/ከተማ ንግድ ጽ/ቤት

3. ቦሌ ክ/ከተማ ንግድ ጽ/ቤት በመሆን የላፕቶፕ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል!


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments