የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶ...

image description
- In ንግደረ    0

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ይበልጥ ለማዘመን የአቅም ግንባታ ስራዎች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሠራ መሆኑን ገለፀ።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ይበልጥ ለማዘመን የአቅም ግንባታ ስራዎች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሠራ መሆኑን ገለፀ።

መጋቢት 21/2018 ዓ ም

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የገበያ ልማት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ደበሌ ቢሮ 19 የሚሆኑ አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ አስደግፎ እየሰጠ እንደሚገኝ ገልፀው የቢሮውን አገልግሎት ይበልጥ ለማሳለጥ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

እንደ ምክትል ቢሮ ኃላፊው ገለፃ ቢሮው በቴክኖሎጂ አስደግፉ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ይበልጥ ለማሳለጥ የፈፃሚውንና የአመራሩን አቅም የመገንባት ስራዎች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሠራ መሆኑን ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ያነጋገራቸው የክ/ከተማ ፈፃሚዎችና ቡድን መሪዎች ቢሮው በተለያዩ ጊዜያት የሚሰጣቸው ስልጠናዎች የሠራተኛውን አቅም ከማሳደግ ባሻገር የአገልግሎት አሰጣጡን በማሳለጥ ረገድ ከፍተኛ ሚና የተጫወቱ መሆናቸውን ገልፀዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments