የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንግድ ግብረ-ኃ...

image description
- In ንግደረ    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንግድ ግብረ-ኃይል የፌደራል መንግስት ባስተላለፈው የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት አፈጻጸም እና በመጪው የትንሳኤ በዓል የምርት አቅርቦትና ቁጥጥር ስራዎች ላይ ውይይት አካሄደ፤

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንግድ ግብረ-ኃይል የፌደራል መንግስት ባስተላለፈው የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት አፈጻጸም እና በመጪው የትንሳኤ በዓል የምርት አቅርቦትና ቁጥጥር ስራዎች ላይ ውይይት አካሄደ፤

መጋቢት 25/2018 ዓ.ም.

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንግድ ግብረ-ኃይል የፌደራል መንግስት በተቀመጠው የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት አቅጣጫ እና በመጪው የትንሳኤ በዓል የምርት አቅርቦትና ቁጥጥር ስራዎች ላይ ሰፊ ውይይት አካሂዷል።

ውይይቱን የመሩት የከተማችን ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ ሲሆኑ፣ የንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ፣ የሠላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊድያ ግርማ እና የተለያዩ ቢሮዎች ኃላፊዎች እንዲሁም የ11 ክፍለ-ከተሞች ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችና የንግድ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

ክቡር አቶ ጃንጥራር፣ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው የሠላም እጦት ያስከተለውን ዓለም አቀፍ የነዳጅ ቀውስ በመጥቀስ፣ መንግስት ችግሩን ለመቋቋም የተለያዩ ስትራቴጂካዊ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን ገልጸዋል። በከተማው ውስጥ ያሉ ሁሉም ማደያዎች የነዳጅ ስርጭትን በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በመከተል ማከናወን እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል።

በዚህ መሠረት የነዳጅ ቅድሚያ አገልግሎት ሊሰጣቸው የሚገቡ ዘርፎች

የነዳጅ መጓጓዣ ቦቴዎች፣ የወጪና ገቢ ምርት ተሽከርካሪዎች፣ የመሰረታዊ ፍጆታና የኤክስፖርት ምርት፣ ኢንዱስትሪዎች፣ ቁልፍ የልማት ፕሮጀክቶች፣ መካናይዝድ እርሻዎች፣ የፀጥታና ደህንነት ተቋማት፣ የህዝብ መጓጓዣ፣ የጤና አገልግሎቶች፣ የቴሌኮም አገልግሎቶች፣ የውሃና መብራት አጣዳፊ ስራዎች፣ የሚዲያና ሰብአዊ አገልግሎቶችእና ብዙ ተማሪዎች ያሉባቸው ዩኒቨርሲቲዎች መሆን እንዳለባቸው እንዲሁም የአቅጣጫው አፈጻጸም በተቀናጀ መልኩ እንዲሆን የጸጥታ አካላትና የሚመለከታቸው ባለድርሻ ተቋማት በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው ተገልጿል።

የመጪው የትንሳኤ በዓል ግብይት ዝግጅትን በተመለከተ፣ የከተማችን ነዋሪዎች የበዓል ምርት ፍላጎትን ለማሟላት ከምርት አቅርቦትና ቁጥጥር አኳያ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ቀርበው በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት ተካሂዶባቸዋል።

በመጨረሻም የበዓል ገበያው የተረጋጋና ሰላማዊ እንዲሆን ሁሉም አካላት በቅንጅት መስራትና ኃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸው አቅጣጫ ተቀምጧል። ኢኮኖሚ፡ ከመሰረተ ልማት ወደ ሰው ሰራሽ አስተውሎት


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments