“ለከተማችን አዲስ አበባ ነዋሪ የግብርና ምርቶችን በጥራትና በብዛት በማቅረብ፣ ፍትሃዊና የተረጋጋ የንግድ ሥርዓት እንዲኖር የድርሻችሁን ልትወጡ ይገባል!” የተከበሩ አቶ ሽመልስ ሀሰኑ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የገበያ ማዕከላት ዘርፍ ኃላፊ
“ለከተማችን አዲስ አበባ ነዋሪ የግብርና ምርቶችን በጥራትና በብዛት በማቅረብ፣ ፍትሃዊና የተረጋጋ የንግድ ሥርዓት እንዲኖር የድርሻችሁን ልትወጡ ይገባል!” የተከበሩ አቶ ሽመልስ ሀሰኑ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የገበያ ማዕከላት ዘርፍ ኃላፊ
=====+++======
ሚያዝያ 27 ቀን 2018 ዓ.ም.
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ሰሚት አካባቢ በተገነባው ዘመናዊ የግብርና ምርቶች መሸጫ የገበያ ማዕከል ውስጥ የሚገኙትን ሱቆች የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በግልጽ ጨረታ ላሸነፉ የጅምላና የችርቻሮ ነጋዴዎች በዛሬው እለት በእጣ አስተላልፏል።
በገበያ ማዕከሉ የሱቆች ማስተላለፍ መርሐግብር ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የገበያ ማዕከላት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሽመልስ ሀሰኑ “ለከተማችን አዲስ አበባ ነዋሪ የግብርና ምርቶችን በጥራትና በብዛት በማቅረብ፣ ፍትሃዊና የተረጋጋ የንግድ ሥርዓት እንዲኖር የድርሻችሁን ልትወጡ ይገባል!” ብለዋል። በዛሬው እለት በእጣ የተላለፉት፤ 16 መጋዘኖች፣ 9 የጅምላ መሸጫ ሱቆችና 87 የችርቻሮ ሱቆች ናቸው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments