የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በወረዳ 08 በህዝብ ተሳትፎ የሰራቸውን የልማት ስራዎችን ለአገልግሎት ክፍት አደረገ
የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በወረዳ 08 በህዝብ ተሳትፎ የሰራቸውን የልማት ስራዎችን ለአገልግሎት ክፍት አደረገ
ፍትሃዊ፣ አካታች እና ተሻጋሪ አገልግሎት በመስጠት የህዝባችንን ችግሮች ለመፍታት በትጋት እየተሰራ መሆኑ ተገልፃል።
ለአገልግሎት ክፍት በተደረጉ የልማት ስራዎች ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ አስተዳደር የንግድ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ እንደገለፁት በክፍለ ከተማው እየተከናወኑ ያሉ የፕሌ ግራውንድ፣ የወጣቶችና የህፃናት የእግር ኳስ መጫወቻ እንዲሁም የአስፓልት ልማት ስራዎች ለህብረተሰቡ የተሻለ የኑሮ ሁኔታ ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ገልፀዋል።
በተለይም ለወጣቶችና ለህፃናት የመዝናኛና የስፖርት ቦታዎችን ማስፋፋት ማህበራዊ ትስስርን ከማጠናከር ባለፈ የወጣቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ በበኩላቸው ፣ለህዝቡ የተገባውን ቃል ለማክበር ከማህበረሰቡ ጋር ቅርብ በመሆን ፍትሃዊና አካታች አገልግሎት ለመስጠት በተለያዩ ዘርፎች ሰፊ የልማት ስራዎች ተከናውኗል በማለት የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ ገልፀዋል።
በተለይም የህብረተሰቡን ውስብስብ ችግሮች በቅርብ በመረዳት እና በመፍታት ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውን ጠቅሰው፣ ይህንንም የበለጠ ለማጠናከር በቀጣይነት ከህዝቡ ጋር ተቀራርቦ የመስራት አቅጣጫ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
ፍትሀዊነት፣ ተጠያቂነት እና የህዝብ ተሳትፎን ማጠናከር ለክፍለ ከተማው የልማት ጉዞ ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments