የሰሚት ሁለገብ ዘመናዊ የገበያ ማዕከል ለምርቃት...

image description
- In ንግደረ    0

የሰሚት ሁለገብ ዘመናዊ የገበያ ማዕከል ለምርቃት ዝግጁ ሆነ!

የሰሚት ሁለገብ ዘመናዊ የገበያ ማዕከል ለምርቃት ዝግጁ ሆነ!

=======++++======

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2018 ዓ.ም.

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ሰሚት አካባቢ፣ያስገነባው ዘመናዊ ሁለገብ የገበያ ማዕከል ለምርቃት ዝግጁ ሆኗል።

ይህ ዘመናዊ የገበያ ማዕከል 9 የጅምላ እና 87 የችርቻሮ መሸጫ ሱቆችን፣ 17 መጋዘኖችን፣ ወፍጮ ቤቶችንና ካፌቴሪያዎችን ከምቹና ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ቦታ ጋር ያሟላ ነው።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ እንደገለጹት “ሁለገብ የገበያ ማዕከሉ ወደስራ ሲገባ የሰሚትና አካባቢው ማህበረሰብ ሁሉንም ዓይነት የሰብል ምርቶች፣ አትክልትና ፍራፍሬዎች፣ ቅመማ-ቅመሞችና የፋብሪካ ምርቶችን በአቅራቢያው በተመጣጣኝ ዋጋ፣ በጥራት እና በብዛት እንዲያገኝ ያስችላል። በተጨማሪም በከተማችን ፍትሃዊና የተረጋጋ የንግድ ሥርዓት እንዲኖር ለሚደረገው ጥረት አጋዥ ይሆናል።”

ወ/ሮ ሀቢባ በተጨማሪም በገበያ ማዕከሉ ለሽያጭ የሚቀርቡ ምርቶች ከመደበኛ ገበያዎች ጋር ሲነጻጸሩ ከ15% እስከ 20% የዋጋ ቅናሽ እንደሚኖራቸው አስገንዝበዋል።

ይህ ፕሮጀክት በተለይ ለደቡባዊ አዲስ አበባ ነዋሪዎች ትልቅ እፎይታ የሚፈጥር ሲሆን፣ መክፈቻው በቅርቡ እንደሚካሄድ ይጠበቃል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments