የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የሪፎርም ስራዎች አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ!
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የሪፎርም ስራዎች አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ!
========+++++=======
ግንቦት 6፣ 2018 ዓ.ም.
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የሪፎርም ስራዎች አፈጻጸም ግምገማ አካሂዷል። ግምገማውን የመሩት የንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ሲሆኑ፣ በግምገማው የቢሮው የሪፎርም ስራዎች የደረሰበትን ደረጃ በዝርዝር ተገምግሟል።
በግምገማ መድረኩ ላይ የቢሮው የፕሮሰስ ካውንስል አባላት፣ የክፍለ ከተሞች ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና ቡድን መሪዎች ተሳትፈዋል።
ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በመድረኩ ላይ፣ የሪፎርም ስራዎች አፈጻጸም በጥሩ ደረጃ ላይ መሆኑን ገልጸው፣ “የተጀመረውን ሪፎርም በማጠናከርና በማዘመን፣ በከተማችን የተደራጀ፣ ዘመናዊና ቀልጣፋ የሲቪል ሰርቫንት ለመፍጠር እንደሚገባ” አሳስበዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments