የሸማቾች መብት ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ባለፉት አስር...

image description
- In ንግደረ    0

የሸማቾች መብት ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ባለፉት አስር ወራት ያከናወናቸው ተግባራት አመርቂ መሆናቸው ተገለጸ!

የሸማቾች መብት ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ባለፉት አስር ወራት ያከናወናቸው ተግባራት አመርቂ መሆናቸው ተገለጸ!

ግንቦት 7፣ 2018 ዓ.ም.

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የሸማቾች መብት ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ባለፉት አስር ወራት የከተማዋን ሸማቾች መብት ከማስጠበቅ አንጻር ያከናወናቸው ተግባራት አመርቂ መሆናቸው ተገለጸ። የሸማቾች መብት ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መሀመድ አላቦ ከዝግጅት ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፣ ዳይሬክቶሬቱ ባለፉት አስር ወራት ሸማቾች በተደራጀ አግባብ መብቶቻቸውን ለማስከበር እንዲችሉ ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል፡፡ ዳይሬክተሩ አክለውም ከሸማቾች በደረሱ ጥቆማዎች መሠረት ጥራታቸውን ያልጠበቁ፣ ለፀሐይና ለብልሽት የተጋለጡ፣ ከደረጃ በታች የሆኑ እንዲሁም የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ምርቶች፣ ምግቦችና መጠጦች ከገበያ እንዲወገዱ ማድረጉን ገልጸዋል።

ቢሮው በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሠረት በ8588 ነፃ የስልክ መስመር በደረሱ ጥቆማዎች መነሻነት፣ በቅዳሜና እሁድ ገበያዎች 40 ነጋዴዎች ከትስስር እንዲወጡ ሲደረግ፣ 139 ነጋዴዎች የመጨረሻ ደረጃ ማስጠንቀቂያ እንዲሁም 179 ነጋዴዎች የመጀመሪያ ደረጃ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል። በተጨማሪም 351 ቅሬታዎች በስልክ እና 296 ቅሬታዎች በአካል ቀርበው ተገቢው ምላሽ እንዲያገኙ መደረጉ ተገልጿል። ዳይሬክቶሬቱ አሳሳች ማስታወቂያዎችን እና የሸማቾችን መብት የሚጎዱ ተግባራትን ለመከላከል የጀመረውን ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ መሀመድ ገልጸዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments