ባለፉት አምስት አመታት በከተማችን አዲስ አበባ የምርት አቅርቦትን ማሳደግና የንግድ ስርዓቱን ማዘመ በመቻሉ የኑሮ ውድነትን መከላከል ተችሏል፡፡
ባለፉት አምስት አመታት በከተማችን አዲስ አበባ የምርት አቅርቦትን ማሳደግና የንግድ ስርዓቱን ማዘመ በመቻሉ የኑሮ ውድነትን መከላከል ተችሏል፡፡
ግንቦት11/2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በልደታ ክ/ከተማ ከሚገኙ የንግድ ማህበረሰብ ጋር በንግድ ዘርፍ ስራዎች አፈፃፀም ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።
ውይይቱን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ፣ የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ እና የልደታ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘመኑ በጋራ መርተውታል።
ከመድረክ ባለፉት አምስት አመታት በንግደ ዘርፍ በተሰሩ ስራዎች የተገኙ ቱርፋቶችን በቢሮው የንግድ ጥናትና ፕሮሞሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት አቶ ሙሰማ ጀማል አቅርበው ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል።
በውይይቱ መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ባለፉት አምስት አመታት 16 የሚሆኑ አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ ኦንላይን እንዲሰጡ በማድረግ ከሙስና የፀዳ ቀልጣፋና ፍትሃዊ አገልግሎት መስጠት ተችሏል ብለዋል።
እንደ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ገለፃ በከተማችን አዲስ አበባ በዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በኑሮ ውድነት እንዳይጎዱ በከተማችን አዲስ አበባ ምርት አቅርቦት ማሳደግ ላይ ትኩረት አድርጎ በመሰራቱ አመርቂ ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል፡፡
የኑሮ ውድነትን ለመከላከል የቀጥታ ግብይት አሰራርን ተግባራዊ በማድረግ ሰው ሰራሽ በሆነ አሰራር የምርት እጥረት እንዲፈጠር በማድረግ የምርቶችን ዋጋ የሚጨምሩ ህገ-ወጥ ደላሎችን ከገያው በማስወጣት ምርቶች ከአምራቹ በቀጥታ ወደ ከተማው የሚገባበትን ሥርዓት ተዘርግቷል ብለዋል።
ባለፉት አመታት የተረጋጋ የገበያ ስርዓት ከመፍጠር አንፃር መንግስት የአደባባይ ላይ ባዶ ቦታዎችን በመፍቀድ እና ከአርሶ አደሩ ጋር ቀጥታ ትስስር በማመቻቸት 259 የእሁድ ገበያዎች ተከፍተው ምርቶችን ከመደበኛው ገበያ 20 በመቶ ቅናሽ ለህብረተሰቡ በመቅረብ ላይ ይገኛሉም ብለዋል፡፡
የእሁድ ገበያዎችን ስራ ከማስጀመር ባሻገር በሸማቾች የህብረት ስራ ማህበራት በኩል ዘይትና ስካርን በድጎማ በማቅረብ በከተማችን አዲስ አበባ የኑሮ ውድነትን ከመከላከል አንፃር ትርጉም ያለው ስራ መሰራቱን ገልፀዋል፡፡
ገበያውን ለማረጋጋት ከተሰሩ ስራዎች መካከል የአዲስ አበባ ንግድ ስራዎች ድርጅት እንዲቋቋም በማድረግ መሰረታዊ ፍጆታ ምርቶችን ከአምራቹ በቀጥታ በመግዛት በአዲስ አበባ ለሚገኙ መሰረታዊ የህረት ስራ ማህበራትና ዩኒየኖች በማሰራጨት እንዲሁም ድርጅቱ ባሉት የመሸጫ ሱቆች አማካኝነት ምርቶችን ከነጻ ገበያው በቀነሰ ዋጋ ማሰራጨት ተችሏል፡፡
ሌላው አነስተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸውን ነዋሪዎች ሊፈትን ይችላል ተብሎ የሚታሰበው የዳቦ ዋጋና አቅርቦት መሆኑን ታሳቢ በማድረግ 29 የዳቦ ማምረቻ ቦታዎችን ለባለሀብቶች 10 ዓመት እንዲገለገሉበት በነፃ መስጠት በመቻሉ ዳቦን በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ ተችሏል ብለዋል፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በመጨረሻም የከተማ አስተዳደሩ ከ15 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ሰባት ዘመናዊና ሁለገብ የገበያ ማዕከላት ተገንብተው የከተማችንን የግብይት ስርዓት ፍትሃዊና የተረጋጋ እንዲሆን ማድረግ ተችሏል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments