በቴክኖሎጂ የታገዘ ቀልጣፋና ፍትሃዊ አገልግሎት ለመስጠት የመንግስት አመራርና ሠራተኛው በየጊዜው አቅሙንማሳደግእንዳለበትተገለፀ።
በቴክኖሎጂ የታገዘ ቀልጣፋና ፍትሃዊ አገልግሎት ለመስጠት የመንግስት አመራርና ሠራተኛው በየጊዜው አቅሙንማሳደግእንዳለበትተገለፀ።
ሰኔ15/2018ዓ/ም
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ከአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ቢሮ ጋር በመተባበር በመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ዙሪያ ለሠራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ህዝቡ ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችል የመንግስት ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥንማሻሻል በማስፈለጉ መንግስት ግልፅ የፖሊሲ አቅጣጫ አስቀምጦ ወደ ስራ መግባቱን ተናግረዋል።
እንደ ወ/ሮ ሀቢባ ገለፃ የከተማ አስተዳደሩ የሚሰጣቸውን አብዛኛዎቹን አገልግሎቶች ዲጂታላይዝ በማድረግ ላይ እንደሚገኝና ፈፃሚውን ለዚህ በሚመጥን ደረጃ ብቃቱን ማሳደግ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራመሆኑንአሳውቀዋል።
ስልጠናው የክፍለ ከተማና የወረዳ ንግድ ፅ/ቤት አመራሮች ግንዛቤ ለማሳደግ የተዘጋጀ መሆኑን የገለፁት ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ የመንግስት ሠራተኛው ከስልጠናዎች ባሻገር በራስ ጥረት በየጊዜው አቅሙን በማሳደግ ጊዜውን የዋጀ አገልግሎት መስጠት እንደሚጠበቅበት ተናግረዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments