የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የሚሰ...

image description
- In 2ኛው ከተማ ዓቀፍ "የኢትዮጵያን ይግዙ"    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ለማዘመንና የሰራተኛውን ብቃት ለማሳደግ በትኩረት እየሠራ እንደሚገኝ ተገለፀ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ለማዘመንና የሰራተኛውን ብቃት ለማሳደግ በትኩረት እየሠራ እንደሚገኝ ተገለፀ።

ሰኔ 22/2018ዓ ም

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ከአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ቢሮ ጋር በመተባበር የንግድ ዘርፍ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ዙሪያ ለሠራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ህዝቡ ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችል የመንግስት ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻልና የሰራተኛውን ብቃት ማሳደግ በማስፈለጉ መንግስት ግልፅ የፖሊሲ አቅጣጫ አስቀምጦ ወደ ስራ መግባቱን ተናግረዋል።

እንደ ወ/ሮ ሀቢባ ገለፃ የከተማ አስተዳደሩ የሚሰጣቸውን አብዛኛዎቹን አገልግሎቶች ዲጂታላይዝ በማድረግ ላይ እንደሚገኝና ፈፃሚውን ለዚህ በሚመጥን ደረጃ ብቃቱን ማሳደግ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን አሳውቀዋል።

ስልጠናው የሰራተኛውን ግንዛቤ ለማሳደግ የተዘጋጀ መሆኑን የገለፁት ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ የመንግስት ሠራተኛው ከስልጠናዎች ባሻገር በራስ ጥረት በየጊዜው አቅሙን በማሳደግ ጊዜውን የዋጀ አገልግሎት መስጠት እንደሚጠበቅበት ተናግረዋል።

በስልጠናው ከማዕከል እስከ ወረዳ የሚገኙ ባለሙያዎች፣ ቡድን መሪዎችና ዳይሬከተሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments