የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሠራተኞችና አመራሮች ተስፋን እንትከል በሚል መሪ ቃል የ2018 ዓ ም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር አካሄዱ።
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሠራተኞችና አመራሮች ተስፋን እንትከል በሚል መሪ ቃል የ2018 ዓ ም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር አካሄዱ።
ሰኔ 23/2018 ዓ ም
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ተስፋን እንትከል በሚል መሪ ቃል በቦሌ ክ/ከተማ ቡልቡላ አካባቢ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር አካሂዷል።
በችግኝ ተከላ መርሃ-ግብሩ በመገኘት አረንጓዴ አሻራቸውን ያኖሩት የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ የምንተክለው ችግኞችን ብቻ ሳይሆን የነገ ተስፋችንን ጭምር ነው ብለዋል።
እንደ ወ/ሮ ሀቢባ ገለፃ ባለፉት 8 አመታት በክቡር ጠቅላይ ሚንስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ ሀሳብ አመንጪነት ባለፉት ስምንት አመታት በተካሄደ ኢትዮጵያን አረንጓዴ የማልበስ ዘመቻ እንደ አገር 48 ቢልዮን የሚሆኑ ችግኞችን በመትከል 2.8% የነበረውን አጠቃላይ የደን ሽፋን 24% ማድረስ መቻሉን አሳውቀዋል።
በመጨረሻም ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይሆን በየጊዜው እየተንከባከቡ ማፅደቅ ከሠራተኛውና ከአመራሩ ይጠበቃል በማለት መልዕክት አስተላልፏል
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments