የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የኦዲት ፎረም የ...

image description
- In ንግደረ    0

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የኦዲት ፎረም የ5 ዓመት ማጠቃለያ ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማና የዕውቅና መድረክ አካሄደ።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የኦዲት ፎረም የ5 ዓመት ማጠቃለያ ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማና የዕውቅና መድረክ አካሄደ።

በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር የኦዲት ፎረሙ ሲያደርግ በቆየው ቁጥጥር በጀት በአግባቡ የታለመለት አላማ ላይ እንዲውል እና ግኝቶችን በማስመለስ ረገድ ያደረገው ጥረት አበረታች ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ገልፀዋል ።

የምክር ቤቱን አቅጣጫ ተቀብለው በኦዲት ፎረሙ ውሳኔ መሰረት ፈጥነው ያረሙ ተቋማት በማመስገን ሌሎቹ በከፊል እና ሙሉ በሙሉ ያላስተካከሉ ተቋማት ወደ ማስተካከያ ስራ እንዲገቡ ያሳሰቡት ክ/ት ወ/ሮ ቡዜና አያይዘውም የእርምት እርምጃ መውሰድ ያልቻሉ በህግ እንዲጠየቁም ፎረሙ አቅጣጫ ማስቀመጡን ጠቁመዋል።

በመጨረሻም የአዲት ግኝቶችን ፈጥኖ በማረም አርአያ ለሆኑ ተቋማት እውቅና ተሰጥቷል።

በዚህም መሰረት

1. አዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት

2. የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ

3. የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ

4. የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን

5. የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ

6. የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ

7. የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ

8.የአዲስ አበባ ከተማ ሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጄንሲ

9. የአዲስ አበባ ከተማ ምግብና መድሐኒት ባለስልጣን

10. የአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት

11. የአዲስ አበባ ከተማ የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ

12. አቃቂ ቃሊቲ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና

13. ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል ምስጋና እና እውቅና ተበርክቶላቸዋል::


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments