በበጀት ዓመቱ አጠቃላይ የከተማችን የግብይት ስር...

image description
- In ንግደረ    0

በበጀት ዓመቱ አጠቃላይ የከተማችን የግብይት ስርዓት ውስጣዊና ውጪያዊ ፈተናዎች ያጋጠሙት ቢሆንም የከተማ አስረዳደሩ እነዚህን ፈተናዎች ታሳቢ ያደረጉ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ተግባራዊ በማድረጉ እንደ ማህበረሰብ ሊያጋጥም ይችል የነበረን የኑሮ ውድነት ጫናን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ተችሏል፡፡

በበጀት ዓመቱ አጠቃላይ የከተማችን የግብይት ስርዓት ውስጣዊና ውጪያዊ ፈተናዎች ያጋጠሙት ቢሆንም የከተማ አስረዳደሩ እነዚህን ፈተናዎች ታሳቢ ያደረጉ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ተግባራዊ በማድረጉ እንደ ማህበረሰብ ሊያጋጥም ይችል የነበረን የኑሮ ውድነት ጫናን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ተችሏል፡፡

ሰኔ 27/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ከኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ በ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ የንግድ ዘርፍ ስራዎችን በላቀ ሁኔታ ለማስፈፀም 24/7 ሲሰራ መቆየቱን ገልፀዋል፡፡

ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓትን ዲጂታላይዝ ማድረግ በመቻሉ ተገልጋዮች በአካል መገኘት ሳይጠበቅባቸው 105,726 አዲስ የንግድ ሥራ ፈቃድ እና 339,784 የንግድ ፈቃድ እድሳት በአጠቃላይ 445,510 ለሚሆኑ ነጋዴዎች አገልግሎት መስጠት ተችሏል ብለዋል፡፡

እንደ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ገለፃ ቢሮው በከተማችን አዲስ አበባ የምርት አቅርቦትን ከማሳደግ አንፃር 3,207,055 ኩ/ል የግብርና ምርቶችን በመንግስት የገበያ ማዕከላት እና 5,440,549 ኩ/ል በቅዳሜና እሁድ ገበያዎች በማቅረብ አጠቃላይ በከተማችን የግብርና ምርት አቅርቦትን 8,647,604 ኩ/ል በማቅረብ የዋጋ ግሽበትና የኑሮ ዉድነትን ማረጋጋት ተችሏል፡፡

የግብይት ስርዓት ፍትሃዊነትን ከማረጋገጥ የንግድ ህገ-ወጥነትን መከላከል አስፈላጊ መሆኑን የተናገሩት ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ በበጀት ዓመቱ በ223,760 የንግድ ድርጅቶች የበር ለበር ቁጥጥር በማደረግ 24,568 ጥፋተኛ ነጋዴዎችን በመለየት እንደ ጥፋታቸው ዓይነትና ክብደት 24,568 ህጋዊና አስተዳራዊ የእርምት እርምጃ በመዉሰድ 20,617 ወደ ህጋዊነት እንዲመለሱ ማድረግ መቻሉን አብራርተዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ በነባር ገበያ ማዕከላት ማስፋፊያ ከማድረግ ባሻገር የሰሚት ዘመናዊና ሁለገብ የገበያ ማዕከል ግንባታውን በማጠናቀቅ ስራ እንዲጀምር ማድረግ የተቻለ መሆኑን በመግለፅ ይህም በከተማችን አዲስ አበባ የዘመናዊ ገበያ ማዕከላት ብዛትን ወደ ሰባት አሳድጎታል ብለዋል፡፡

ከገበያ ማእከላት ባሻገር በበጀት አመቱ ተጨማሪ 36 የሰንበት ገበያዎችን ወደ ስራ በማስገባት በከተማችን አዲስ አበባ የሰንበት ገበያ መዳረሻዎችን 256 ማድረስ የተቻለ ሲሆን ይህም የከተማችን ነዋሪዎች የተለያዩ የፍጆታ ምርቶችን በየአካባቢያቸው እስከ 20 በመቶ በሚሆን ቅናሽ መሸመት መቻላቸው የኑሮ ውድነት በመከላከል ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ አጠቃላይ የከተማችን የግብይት ስርዓት ውስጣዊና ውጪያዊ ፈተናዎች ያጋጠሙት ቢሆንም የከተማ አስረዳደሩ እነዚህን ፈተናዎች ታሳቢ ያደረጉ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ተግባራዊ በማድረጉ እንደ ማህበረሰብ ሊያጋጥም ይችል የነበረን የኑሮ ውድነት ጫናን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ መቻሉን ገልፀዋል፡፡

መንግስት የኑሮ ውድነትን ለመከላከልና ፍትሃዊ የንግድ ስርዓት ከማስፈን አንፃር በግብይት ሂደት የደላሎችን ጣልቃ ገብነት ለማስቀረት የተሰሩ ስራዎች ውጤት የተመዘገበባቸው ቢሆንም አሁን የደላሎቹ ጣልቃ ገብነት በሚፈለገው ደረጃ የከሰመ ባለመሆኑ በቀጣይ ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ደላሎችን ሙሉ በሙሉ ከግብይት ስርዓቱ ለማስወጣት በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments