በአዲስ አበባ ከተማ የገቢያ ማረጋጋት፣ የኑሮ ውድነት፣ ህገ-ወጥ ንግድ ቁጥጥርና የ"ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ ግብረ ኃይል በሰኔ ወር ያከናወናቸውን የሥራ ክንውኖች በጋራ ገምግሟል።
በአዲስ አበባ ከተማ የገቢያ ማረጋጋት፣ የኑሮ ውድነት፣ ህገ-ወጥ ንግድ ቁጥጥርና የ"ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ ግብረ ኃይል በሰኔ ወር ያከናወናቸውን የሥራ ክንውኖች በጋራ ገምግሟል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የግብ ኃይሉ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ፣ በሰኔ ወር የተከናወኑትን ተግባራት አስመልክቶ ማብራሪያና የቀጣይ አቅጣጫዎችን ሰጥተዋል። በዚሁ መሠረት በከተማ ደረጃ የተከናወኑ የሥራ ክንውኖችን፣ የታዩ ጠንካራ ጎኖችንና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን በዝርዝር ገምግመዋል።
አቶ ጃንጥራር በማብራሪያቸው እንደገለጹት፣ አንዳንድ ክፍለ ከተሞች እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ድረስ ያለውን የገበያ መረጋጋት ዝግጅት ለመደገፍና የአምራቾችንና የአቅራቢዎችን አቅም ለማቀናጀት የተሻለና ጠንካራ ሥራ ማከናወናቸውን ገልጸዋል።
በዚህ ግምገማ መሠረት፣ የገበያ ማረጋጋት ሥራው አፈጻጸም ምን እንደሚመስል፣ የግብይት ትስስር መፍጠርና የዋጋ ንረትን ማቃለል እንዲሁም ሕገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን መቆጣጠር ላይ የተሰሩ ሥራዎች በዝርዝር ተፈትሸዋል።
አሁን ያለውን አፈጻጸም በጥልቀት በመገምገም፣ በተለይም በቀጣይነት ተጨማሪ ትኩረት ሊሰጣቸው በሚገቡ ጉዳዮች ላይ ማለትም በአቅርቦትና ፍላጎት ማመጣጠን፣ የግብይት ሰንሰለትን ማስተካከልና ቁጥጥርን ማጠናከር ላይ ግብረ ኃይሉ የጋራ መግባባት ላይ ደርሷል።
የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራ በበኩላቸው የምርት አቅርቦትን በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ በከተማዋ ይታይ የነበረውን የዋጋ ንረት ማረጋጋት መቻሉን ተናግረዋል።
የንግድ ቢሮው ከተለያዩ ክፍለ ከተሞችና ከግብረ ኃይሉ ጋር በመቀናጀት የአቅርቦት ጉድለት እንዳይፈጠር በየሳምንቱ ጠንካራ የክትትልና የቁጥጥር ሥራዎችን ሲያከናውን እንደቆየ ወ/ሮ ሀቢባ ተናግረዋል።
እነዚህን ነጥቦች መነሻ በማድረግም በቀጣይም ይህንን የተጀመረውን የምርት አቅርቦት የማሳደግና ሕገ-ወጥ የዋጋ ጭማሪን የመቆጣጠር ተግባር አጠናክሮ በመቀጠል የነዋሪውን የኑሮ ጫና ለማቃለል በትኩረት እንደሚሠራ የግብረ ኃይሉ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ጃንጥራር የቀጣይ የሥራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments