በሀዋሳ ከተማ የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ የተ...

image description
- In ንግደረ    0

በሀዋሳ ከተማ የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ የተቋቋመ ግብረ ኃይል በአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የልምድ ልውውጥ አካሄደ::

በሀዋሳ ከተማ የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ የተቋቋመ ግብረ ኃይል በአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የልምድ ልውውጥ አካሄደ::

ሐምሌ 16/2018 ዓ.ም.

በሀዋሳ ከተማ የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ የተቋቋመ ግብረ-ኃይል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በመገኘት የልምድ ልውውጥ አካሂዷል። የልምድ ልውውጡን ለመቀመር ለመጣው ግብረ-ኃይል ገለጻ ያደረጉት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የግብይት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ጸጋዬ ደበሌ፣ የገበያ ማዕከላትን በማልማት አምራቾችንና ቸርቻሪ ነጋዴዎችን ወደ ማዕከላቱ በማስገባት፣ የቅዳሜና እሁድ ገበያዎችን በማደራጀትና በመላ ከተማው በማስፋፋት፣ እንዲሁም የመሠረታዊ ሸቀጦችን በድጎማ በማቅረብ የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች አብራርተዋል።

በልምድ ልውውጡ ወቅት የግብረ-ኃይሉ ሰብሳቢና የሀዋሳ ከተማ ህብረት ሥራ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ክፍሌ ዋሬ እንደገለጹት፣ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ የሚያግዙና ለሀዋሳ ከተማም ሆነ ለሌሎች የሀገራችን ከተሞች አርዓያ ሊሆኑ የሚችሉ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል። አቶ ክፍሌ አክለውም፣ ሀዋሳ ከተማ ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የተገኘውን ልምድ በመቀመርና በማስፋት የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ የሚያግዙ ተግባራትን እንደሚያጠናክር ገልጸዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments