"የከተማችንን ነዋሪ የኑሮ ጫናን ለማቅለል መረባ...

image description
- In ንግደረ    0

"የከተማችንን ነዋሪ የኑሮ ጫናን ለማቅለል መረባረብ የሁላችንም ኃላፊነት ነው።" ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ኃላፊ

"የከተማችንን ነዋሪ የኑሮ ጫናን ለማቅለል መረባረብ የሁላችንም ኃላፊነት ነው።" ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ኃላፊ ነሐሴ 01/2018 ዓ.ም. አዲስ አበባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ፣ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ካቋቋመው ከሸገር ዳቦ ፋብሪካና ከዳቦ ሻጭ ማህበራት ጋር በ2018 በጀት ዓመት የሸገር ዳቦ ምርት አቅርቦት ዕቅድ አፈጻጸም፣ በሂደቱ የታዩ ክፍተቶችና በ2019 በጀት ዓመት ሊወሰዱ በሚገባቸው የእርምት እርምጃዎች ዙሪያ የግምገማ መድረክ አካሂዷል። በመድረኩ ላይ የሸገር ዳቦ ምርትና ስርጭት አፈጻጸም፣ የምርት ሁኔታ እንዲሁም ለሕብረተሰቡ ያለውን ተደራሽነትና የተገኙ ውጤቶች ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል። የመድረኩ ተሳታፊ ማህበራት በግምገማው ወቅት በአንዳንድ አካባቢዎች የምርት እጥረት፣ የስርጭት መጓተት፣ የመረጃ ፍሰት ክፍተት እና የክትትል ድክመቶች መኖራቸውን ጠቁመል። እነዚህን ችግሮች በመፍታት የምርቱን ተደራሽነት ለማሻሻል የሁሉም አካላት የተቀናጀ ሥራ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል። የሸገር ዳቦ ፋብሪካ አመራሮች በበኩላቸው፣ ፋብሪካው በቀን እስከ 1.5 ሚሊዮን ዳቦ የማምረት አቅም ቢኖረውም፣ በጥሬ ዕቃ እጥረትና በግብዓቶች የዋጋ ንረት ምክንያት በሙሉ አቅሙ ማምረት እንዳልቻለ ገልጸዋል። ችግሩን ለመቅረፍ በመንግሥት፣ በፋብሪካውና በሌሎች ተዋናዮች መካከል የተጠናከረ ቅንጅት እንደሚያስፈልግም አስረድተዋል። በግምገማው ማጠቃለያም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ፣ የምርት አቅርቦትን ማሳደግ፣ የስርጭት ሥርዓቱን ማጠናከር፣ የክትትልና ቁጥጥር ሥርዓቱን ማሻሻል፣ በሁሉም መሸጫ ቦታዎች ፍትሃዊ ስርጭትን ማረጋገጥ እና የተቋማትን ቅንጅት ማጠናከር የሚያስችሉ የእርምት እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። በመጨረሻም ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ "የነዋሪውን የኑሮ ጫና ለማቅለል መረባረብ የሁላችንም ኃላፊነት ነው፤ ሁሉም ተዋናዮች የተቀመጡትን አቅጣጫዎች በተጠያቂነት በመፈጸም የሸገር ዳቦ ምርትና አቅርቦት የተረጋጋ፣ ፍትሃዊ እና ለሕብረተሰቡ ተደራሽ እንዲሆን በቅንጅት እንስራ!" የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።

Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments