"በከተማችን አዲስ አበባ የፍጆታ አቅርቦትን በማ...

image description
- In ንግደረ    0

"በከተማችን አዲስ አበባ የፍጆታ አቅርቦትን በማሳደግ ገበያውን ማረጋጋትና የኑሮ ውድነትን መከላከል ተችሏል"። ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ:- የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ

"በከተማችን አዲስ አበባ የፍጆታ አቅርቦትን በማሳደግ ገበያውን ማረጋጋትና የኑሮ ውድነትን መከላከል ተችሏል"። ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ:- የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ

ነሀሴ 07/2018 ዓ ም

የአዲስ አበባ የገበያ ማረጋጋት ህገ ወጥ ንግድ ቁጥጥርና የኢትዮጵያ አዲስ አበባ ታምርት ግብረ ኃይል ገበያውን ከማረጋጋት አንፃር ባለፉት ሁለት ወራት የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።

በግብረ-ኃይሉ ባለፉት ሁለት ወራት የተከናወኑ ተግባራት ከመድረክ ከቀረበ በኋላ ከተሳታፊዎች በተሠሩ ስራዎች የመጡ ለውጦች በስራ ሂደት ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ተነስተው ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

በውይይቱ ማጠቃለያ ሀሳባቸውን የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ "በከተማችን አዲስ አበባ የፍጆታ አቅርቦትን ማሳደግና ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን መከላከል በመቻሉ ገበያውን ማረጋጋትና የኑሮ ውድነትን ትርጉም ባለው መንገድ መከላከል ተችሏል ብለዋል።

እንደ ክቡር አቶ ጃንጥራር ገለፃ የንግድ ስርዓቱን ፍትሀዊነት በማረጋገጥ ረገድ የተሠሩ ስራዎች ውጤት ያስመዘገቡ ቢሆንም ገበያውን በዘላቂነት ለማረጋጋት አሁንም በየደረጃው የሚገኙ የግብረ-ኃይሉ አባላት በጥብቅ ዲሲፕሊን ተቀናጅተው 24/7 ሊሠሩ ይገባል ብለዋል።

የግብረ-ኃይሉ ምክትል ሰብሳቢና የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ከአቅርቦት አንፃር በአትክልትና ፍራፍሬ የመጣውን ውጤት አመርቂ መሆኑን ገልፀው የሰብል፣ የወተት ተዋፅኦ እና የኢንዱስትሪ ምርቶች አቅርቦትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

በመድረኩ የተገኙት የግብረ-ኃይሉ ፀሀፊና የአዲስ አበባ ጸጥታና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን በመከላከል የግብይት ሂደቱን ፍትሃዊነት በማረጋገጥ ረገድ የተሠራው ስራ ውጤታማ መሆኑን ገልፀዋል።

በመድረኩ ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ የሚገኙ የገበያ ማረጋጋት፣ ህገ-ወጥ የንግድ ቁጥጥርና የኢትዮጵያ/አዲስ አበባ ታምርት ግብረ-ኃይል አባላት ተሳትፈዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments