መጪዎችን የመስቀልና የእሬቻ በዓላት ምክንያት በ...

image description
- In ንግደረ    0

መጪዎችን የመስቀልና የእሬቻ በዓላት ምክንያት በማድረግ በከተማችን አዲስ አበባ ሊፈፀሙ የሚችሉ ማናቸውም ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን ለመከላከል የቁጥጥር ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገለፀ።

መጪዎችን የመስቀልና የእሬቻ በዓላት ምክንያት በማድረግ በከተማችን አዲስ አበባ ሊፈፀሙ የሚችሉ ማናቸውም ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን ለመከላከል የቁጥጥር ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገለፀ።

መስከረም 08/2019 ዓ ም

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የግብይት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ደበሌ ከዝግጅት ክፍላችን ጋር በነበራቸው ቆይታ መጪውን የመሰቀልና የኢሬቻ በዓላት ምክንያት በማድረግ የምርት እጥረት እንዳይፈጠር ከክልሎች እና ከአጎራባች ከተሞች ጋር በቅርበት ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው ለዚህም በቂ የበዓል ፍጆታ ምርቶች መዘጋጀታቸውን አሳውቀዋል።

አቶ ፀጋዬ አክለውም ከነገ 09/01/19 ቀን ጀምሮ በዓሉን በማስመልከት በከተማችን የሚገኙ የሰንበት ገበያዎች ሳምንቱን ሙሉ ለሸማቾች ክፍት እንደሚሆኑ ተናግረዋል።

በዓሉን ምክንያት በማድረግ አርቴፊሻል የሆነ የዋጋ ንረት እንዳይፈጠር የቁጥጥር ስራው ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ያሳወቁት አቶ ፀጋዬ በየደረጃው የሚገኙ የህገ-ወጥ ንግድ መከላከልና የገበያ ማረጋጋት ግብረ-ኃይል አባላት ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት ይሰራሉ ብለዋል።

እንደ አቶ ፀጋዬ ገለፃ የበዓል ፍጆታ ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ በቂ ዝግጅት መደረጉን አስታውቀው፣ ህገ-ወጥ የሆነ ማንኛውም የንግድ እንቅስቃሴ ሲያጋጥም የከተማችን ነዋሪ በ8588 ነፃ የስልክ ጥሪ በመደወል ጥቆማ መስጠት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments