
ከተማ አቀፉ ህዝባዊ ኮንፈረንስ በሁለተኛው የብልፅግና ፓርቲ ጉባዔ አቅጣጫዎች ላይ የጋራ ግንዛቤ እና ተግባቦት ፈጥሮ ተጠናቋል!
ከተማ አቀፉ ህዝባዊ ኮንፈረንስ በሁለተኛው የብልፅግና ፓርቲ ጉባዔ አቅጣጫዎች ላይ የጋራ ግንዛቤ እና ተግባቦት ፈጥሮ ተጠናቋል!
በብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እና ም/ቤት አባላት የተመራው ሀገር አቀፍ የህዝብ ኮንፈረንስ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ አባገዳዎች ፣ ወጣቶች ፣ ሴቶች ፣ የፓርቲያችን አባላት እና ደጋፊዎች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት በከተማ ደረጃ የተካሄደ ሲሆን በፓርቲያችን አቅጣጫዎች ዙሪያ የጋራ ተግባቦት መፍጠር አስችሏል።
የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ አለሚቱ ኡመድ ለከተማ አቀፍ ውይይቱ የተዘጋጀውን መነሻ ፅሁፍ ያቀረቡ ሲሆን ከተሳታፊዎች በተነሱ ሀሳቦችም ዳብሯል።
የህዝባችን ተሳትፎ አጠናክረን ፣ ተግዳሮቶችን እየተሻገርን ፣ ፈተናን ወደ ድል እየቀየርን ወደ ፊት መራመድ ግድ ይለናል ያሉት ወ/ሮ አለሚቱ ፓርቲያችን በሁለተኛው መደበኛ ጉባዔው ያሳለፋቸውን ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች በቁርጠኝነት ለመፈፀም ቃልአችንን አድሰናል ብለዋል።
ጠንካራ ፓርቲ በመገንባት የሀገረ መንግስት ግንባታውን ለማጠናከር ጥራት ያለው የአባል ምልመላን ጨምሮ የአመራሩንና የአባላትን የአመለካከትና የተግባር አንድነት በማጠናከር ፣ ጠንካራ ኢንስፔክሽን በማካሄድ ቃልን አልቆ ለመፈፀም ብርቱ ጥረት እንደሚደረግ አስገንዝበዋል።
ነፃ እና ገለልተኛ ተቋማትን ለመገንባት የተጀመሩ መሰረታዊ ስራዎችን በማፅነት የፍትህ ስርዓቱን ይበልጥ ለማሻሻልም ርብርብ እንደሚደረግ አስረድተዋል፡፡
ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ስኬታማነት ፣ ለሽግግር ፍትህ ስርዓቱ ውጤታማነት ሁሉም የድርሻውን በማሳረፍ የሀገር ግንባታውን ማፋጠን እንደሚገባም ተጠቅሷል።
የኢኮኖሚ ዕድገቱን ማፋጠን በብልፅግና ፓርቲ ጉባዔ ልዩ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ መሆኑን ያመላከቱት ርዕሰ መስተዳድሯ፣ ለጋራ ሀገራዊ ዕድገቱ የአጎራባች ክልሎች ቅንጅት ይበልጥ እንዲጠናክር ይሰራል ብለዋል።
የወጣቶችን እና የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተቀናጀ እንቅስቃሴ እንደሚደረግ የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሯ በቀጣይ 9 ነጥብ 15 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር እንደሚሰራ አስገንዝበዋል።
ለሀገራችን መልማት ዕምቅ አቅም የሆነውን የቱሪዝም ዘርፍ ለማነቃቃት እንደ ሀገር የተጀመረው ውጤማ ርብርብ ይበልጥ እንደሚጠናከርም ተመላክቷል።
ከብልሹ አሰራር የተላቀቀ ስኬታማ ሲቪል ሰርቪስ በመገንባት አገልግሎት አሰጣጡ ላይ እመርታ ለማስመዝገብም በቴክኖሎጂ የታገዘ ብርቱ ጥረት ይደረጋል ተብሏል።
ለሀገር ግንባታ ፣ ገዥ ትርክትን ለማስረፅ ፣ የኢትዮጵያን እውነታ ለመግለፅ ውጤታማ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራ ማከናወን የፓርቲያችንም አቅጣጫ በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ማህበራዊ ሚዲያውን ለሀገር ግንባታ በማዋል የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባም ተገልጿል።
የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር እንዳሻው ጣሰው በህዝባዊ ኮንፈረንሱ ላይ እንደተናገሩት ከቃል እስከ ባህል በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ሁለተኛው የብልፅግና ፓርቲ ጉባኤ ምን አቅደን ምን አሳካን ፣ምን ገጠመን ፣ እንዴት ተሻገርነው የሚሉ ጉዳዮች በጥልቀት መገምገማቸውን ጠቅሰዋል።
ከጉባዔው ተሳታፊ አመራርና አባላት በተጨማሪ ፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች ፣ ተጋባዥ እንግዶች እንዲሁም በርካታ የውጭ ሀገር እህት ፓርቲ አመራሮችም ጭምር በተገኙበት የተካሄደው የፓርቲው ጉባዔ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የስራ አስፈፃሚ እና የምክር ቤት አባላት ምርጫ እንደተካሄደበትና ሀገራችንን
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments