የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ እና የአዲስ አበባ ንግ...

image description
- In ንግደረ    0

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ እና የአዲስ አበባ ንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አመራሮች የአዲስ ዓለም-አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከልን ጎበኙ፡፡

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ እና የአዲስ አበባ ንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አመራሮች የአዲስ ዓለም-አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከልን ጎበኙ፡፡

አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የካቲት 24/2017 ዓ.ም

በጉብኝቱ ወቅት ማዕከሉ አለምአቀፋዊ ኮንፍረንሶችን፣ የንግድ ውይይቶችንና ስምምነቶችን፣ ባህላዊ መድረኮችንና ልዩ ልዩ ኤግዚቢሽኖችን ለማስተናገድ እንዲሁም አዳዲስ ሃሳቦች የሚንሸራሸሩበት የንግድና የኢኮኖሚ ስምምነቶች የሚጎለብቱበት ፤ 15ሺ ካሬ የውጪ ሁነት ማስተናገጃ ቦታ ያለው የአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማእከል ባለ 5 ኮከብ ዘመናዊ ሆቴል፣ ሪስቶራንቶች፣ የስፖርት፣ የጤና፣ የመዝናኛ እና የልዩ ልዩ አገልግሎት መስጫን ያከተተ ግዙፍ ማዕከል መሆኑን እና በአንድ ጊዜ እስከ 2000 ተሽከርካሪዎችን ማቆም የሚችል ፓርኪንግ ያለዉ ሲሆን የለሚ ፓርክ እና በቀጥታ ከአየር መንገድ ጋር የሚያገናኝ ሰፊ የመንገድ መሰረተ ልማትም ከማዕከሉ ጋር ተያይዞ በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን ይህም ኢኮኖሚያችንን የሚያነቃቃ፣ ሰፊ የስራ እድል የሚፈጥር ከመሆኑ በላይ እንግዶች ሲመጡ ያለምንም እንግልት ሁሉንም አገልግሎቶች በአንድ ስፍራ እንዲያገኙ ተደርጎ የተሰራ ስለመሆኑ ለጎብኚዎቹ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

አመራሮቹም ለከተማዋ ብሎም ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ትልቅ አበርክትቆ የሚኖረውን ማዕከል እንዲጎበኙ በመደረጉ ደስተኛ መሆናቸውን ጠቅሰው ቢሮውም ሆነ ምክር ቤቱ ሙሉ አቅማቸውን በማስተባበር የንግዱ ማህበረሰብ በማዕከሉ ተሳታፊና ተጠቃሚነቱ እንዲረጋገጥ በትጋት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments