በንግድ ውድድር እና የሸማቾች መብት ጥበቃ አዋጅ...

image description
- In ንግደረ    0

በንግድ ውድድር እና የሸማቾች መብት ጥበቃ አዋጅ 813/2006 ላይ በየደረጃወ ላሉ ቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎች ስልጠና ሠጠ፡

በንግድ ውድድር እና የሸማቾች መብት ጥበቃ አዋጅ 813/2006 ላይ በየደረጃወ ላሉ ቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎች ስልጠና ሠጠ፡፡

አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የካቲት 24/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የሸማቾች መብት ጥበቃ ዳይሬክቶሬት በንግድ ውድድር እና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ 813/2006 እና የሲቪክ ማህበራት ሚና ላይ በየደረጃወ ላሉ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ስልጠና ሰጥቷል፡፡ የስልጠና ሰነዱን ያቀረቡት የዳይሬክቶሬቱ የስራ ባልደረባ አቶ ብርሀኑ ተገኝ በአዋጁ የተካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮችንና የሲቪክ ማህበራትን ሚና በዝርዝረ ለሰልጣኙኞቹ አቅርበዋል፡፡ በውይይት ላይ ለተነሱ ዋና ዋና ጥያቄዎች የሸማቾች መብት ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰፋለም አቦረዳኝ ማብራሪያዎችን የሰጡ ሲሆን አክለውም የሸማቹን መብት ለማስተበቅ እና ፍትሀዊ የንግድ ውድድር ለማስፈን እና የሲቪክ ማህበራት ሚናቸውን እንዲወጡ ከማድረግ አንጻር በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ጠቅሰው ይህም ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ለሰልጣኞቹ መልዕክታቸው አስተላልፈዋል፡፡

በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ንግድ ቢ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች የሸማቾች መብት ጥበቃ አዋጅንና እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ከማስተዋወቅ በተጨማሪም በአራት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥተው ተግባራትን ማከናወን እንደሚገባቸው ያብራሩ ሲሆን እነ,ዚህም ማህበረሰቡን በታማኝነት ማገልገል፤ ሌብነትና ብልሹ አሰራርን መታገል፤ የተገልጋዮችን እርካታ ከፍ ማድረግ እና የኑሮ ውድነቱን ለማቃለል በከተማ አስተዳደሩ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት በአገባቡ መፈጸማቸውን በመከታተል በሂደቱም የሸማቹ መብት መጠበቁን ማረጋገጥ ላይ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አጽንዎት ሰጥተው አሳስበዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments