ቢሮው ከነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያ አመራሮች፣ ከማደ...

image description
- In ንግደረ    0

ቢሮው ከነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያ አመራሮች፣ ከማደያ ባለቤቶች እና ስራ አስኪያጆች ጋራ ውይይት አካሄደ፡፡

ቢሮው ከነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያ አመራሮች፣ ከማደያ ባለቤቶች እና ስራ አስኪያጆች ጋራ ውይይት አካሄደ፡፡

አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የካቲት 27/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበበባ ንግድ ቢሮ በህዝብ ተወካዮች ምክርት ቤት በጸደቀውና በቀጣይ ጊዜያት ተግባራዊ በሚደረገው የነዳጅ አቅርቦት እና ስርጭት በሚደነግገው አዋጅ ላይ ለነዳጅ አቅራቢ ኩባንያዎች ለነዳጅ ማደያ ባለቤቶችን እና ስራ አስኪያጆች በአዋጁ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት አካሂዳል ፡፡

ከተደረገው ገለጻ መናሻነትም ተሳታፊዎቹ ጥያቄና አስተያየት አቅርበዋል በተለይ ነዳጅን በኮንትሮባንድ ማዘዋወር፣ በኤሌክተሮኒክስ ሽያጭ እና መሰል ጉዳዮችን አንስተው በሚመለከጀታቸው የስራ ሀላፊዎች ማብራሪያ ተሰጥቷል በውይይቱ አዋጁ ጠንከር ብሎ የተዘጋጀ መሆኑ እና ህገወ-ጥነትን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ውጤታማ እንደሚያደርገው ተሳታፊዎቹ ገልጸው ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት በሁሉም ደረጃ አገልግሎቱ ላይ ለሚሳተፉ አካላት ተመሳሳይ የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረኮች መካሄድ እንደሚገባቸው አንስተዋል፡፡

በተያያዘም የነዳጅ ማደያ ባለቤቶች ጋር በተደረገው ውይይት ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን በመወጣት ረገድ በርካታ ተግባራትን እያከናወኑ መሆኑ አንስተው በዚህም ዓመት ቢሮው የአቅመ ደካሞችን ቤት ለማደስ የሚያስችል ዕቅድ ያቀረበ ሲሆን የማደያ ባለቤቶቹም በቀረበው ዕቅድ ደስተኛ መሆናቸውን እና የሚጠበቅባቸውን ኃላነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments