የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ሀላፊ...

image description
- In ንግደረ    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በልደታ ክ/ከተማ የሚገኝ የእሁድ ገበያዎችንና የበዓል ባዛሮችን ጎበኙ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በልደታ ክ/ከተማ የሚገኝ የእሁድ ገበያዎችንና የበዓል ባዛሮችን ጎበኙ

አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ መጋቢት 20/2017 ዓ/ም

ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅና የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ (የኢድ አል -ፈጥር በዓል ) ባዛር የምርት አቅርቦት እና የዋጋ ሁኔታ ተመልክተዋል።

በምልከታው ለበዓሉ አስፈላጊ የሆኑ የኢንዱስትሪና የግብርና ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቹ መቅረቡን ያረጋገጡት ወ/ሮ ሀቢባ አስተዳደሩ የምርት እጥረትና በዓሉን አስመልክቶ የዋጋ ጭማሪ እንዳይከሰት እያደረገ ያለው ክትትል ተጠናክሮ እንዲቀጥልም አሳስበዋል።

ወ/ሮ ሀቢባ አክለውም ማህበረሰቡ በአቅራቢያው ባሉ የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች እንዲሁም ባዛሮች በመገኘት ምርቶችን በመሸመት በዓሉን እንዲያሳልፍ ጥሪ አስተላልፈዋል።

የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ በቅዳሜና እሁድ ገብያዎችና በበዓል ባዛሮች ጥራት ያላቸው ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርቡ ለማድረግ የክትትል ስራችንን አጠናክረን እየሰራን ነው ብለዋል።

በቅዳሜና እሁድ ገበያዎች እንዲሁም በበዓል ባዛሮች የምርት አቅርቦት እንዳይከሰት የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎችንም አከናውነናል ብለዋል ወ/ሮ አበባ።

ሸማቾች በበኩላቸው ጥራት ያላቸውን ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እየሸመተ ነው ብለው አስተዳደሩ የዋጋ ጭማሪ እና የምርት እጥረት እንዳይከሰት እያደረገ ላለው የክትትል ና ድጋፍ ስራም ምስጋና አቅርበዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments