
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ንግድ ጽ/ቤት መደበኛ ያልሆነ ንግድን ስርዓት ለማስያዝ በወጣው ደንብ ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል::
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ንግድ ጽ/ቤት መደበኛ ያልሆነ ንግድን ስርዓት ለማስያዝ በወጣው ደንብ ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል::
አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ መጋቢት 23/2017 ዓ.ም
የክፍለ ከተማው ንግድ ጽ/ቤት መደበኛ ያልሆነ ንግድ ስርዓት ማስያዝ በተሻሻለው በመደበኛ ያልሆነ የጎዳና ላይ ንግድ ስርዓት ማስያዝ ደንብ ዙሪያ እና ኃላፊዎች ባለሙያዎች ባሉበት ዉይይት አድርጓል።
በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ መደበኛ ያልሆነ የጎዳና ላይ ንግድ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ መምጣቱ በመደበኛው የንግድ ሥርዓት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እየፈጠረ መሆኑን በመገንዘብ ይህንን ማስተካክል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ አዋጁ መውጣቱ ተገልጿል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ እንደተናገሩት መደበኛ ያልሆነ የጎዳና ላይ ንግድ በሥርዓት ካልተመራ በከተማ ውበትና ገጽታ በከተማ ጽዳት፡ በትራፊክ ፍሰትና እንቅስቃሴ፣ በኮንትሮባንድ ንግድ መስፋፋት እና በከተማዋ ሰላምና ፀጥታ አጠባበቅ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ችግር የሚያስከትል ሲሆን በደንብና በመመሪያ መተዳደሩ ነጋዴዉም ግንዛቤ እንዲኖረዉ ማድረግ የጎላ ጥቅም እንዳለዉ ተናግረዋል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንዱዓለም ክብረት በበኩላቸው መደበኛ ያልሆነ የጎዳና ላይ ንግድ የሚያስገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ማግኘትና የሚያስከትላቸውን ችግሮች መቅረፍ የሚቻለው ዘርፉ ህጋዊ ሆኖ በሥርዓት ሊመራ በመሆኑና ዘርፉን ሥርዓት በማስያዝ በዘርፉ የተሰማሩ ሰዎች ወደ መደበኛ የንግድ ሥርዓት የሚገቡብትን መንገድ ማመቻቸት አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ህግ ቡደን አስተባባሪ አቶ መለስ ተገኑ፣ መደበኛ ያልሆነ የጎዳና ላይ ንግድን ስርዓት ለማስያዝ የወጣውን ደንብ ቁጥር 184/2017 እና ማንዋል ሰነድ አቅርበዋል፡፡
በዚህም የወጣውን ደንብ እና መመሪያ አክብሮ መስራት ከንግዱ ማህበረሰብ እንደሚጠበቅ መናገራቸውን ተናግረዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments